ፈጣኑ አጥቂ ከአንጋፋው ክለብ ጋር ለመለያየት ከጫፍ ደርሷል።
ከአቃቂ ቃሊቲ እግርኳስን ከጀመረው በኋላ በሐረር ሲቲ ፣ ደደቢት ፣ ፋሲል ከነማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ በመጫወት ወደ ግብፅ ሊግ በማምራትም ዜድ በተባለ ክለብ ውስጥ የአንድ አመት ከስድስት ወራት ቆይታን አድርጎ በድጋሚ ወደ ሀገር ውስጥ በመምጣት ለመቻል ከፈረመ በኋላ በመጨረሻም ግን ወደ ግብፅ ከማምራቱ በፊት የሊጉን ዋንጫ በማንሳት ታሪክ ወደ ሠራበት ቅዱስ ጊዮርጊስ ተመልሶ ፊርማውን በማኖር ያለፉትን ወራቶች በክለቡ እየተጫወተ የፕሪምየር ሊጉ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ዝርዝር ውስጥ በ8 ጎሎች ተቀምጦ ይገኛል።
በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት ውል ቢኖረውም ክለቡ የገባለትን ቃል መፈፀም ባለ መቻሉ ከክለቡ ጋር በሁለተኛው ዙር ሙሉ በሙሉ የሌለው ፈጣኑ አጥቂ ምንም ደመወዝ እያገኘ ባለመሆኑ እንዲሁም ክለቡ የገባውን ቃል ባለ መፈፀሙ እና ምላሽ የሚሰጠውን አካል ማግኘት ባለ መቻሉ ለመለያየት መቃረቡን በሰበሰብኳቸው መረጃዎች ለማረጋገጥ ችያለሁ።
በተደጋጋሚ የፋይናንስ ጥያቄዎች መነሻነት እየተንገዳገደ የሚገኘው አንጋፋው ክለብ ከአቤል ጉዳይ ባለፈ የመፍረስ አደጋ እንደተጋረጠበት ተሰምቷል።


