By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: መድን ከአምስት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል
Share
Notification Show More
Latest News
ሀዋሳ ከተማ ወጣቱን የቀድሞው የግብ ዘቡን አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች ሀዋሳ ከተማ
ወልዋሎዎች አማካዩን የግላቸው አደረጉ
ወልዋሎ ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች
ሀዋሳ ከተማ ሁለገቡን ተጫዋች አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች ሀዋሳ ከተማ
ድሬዳዋ ከተማ ወሳኝ ድል ሲቀናጅ ሀድያ ሆሳዕና እና አዳማ ነጥብ ተጋሩ
ድሬዳዋ ከተማ አዳማ ከተማ መቐለ 70 እንደርታ ሀዲያ ሆሳዕና የጨዋታ ዘገባ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች
ሲዳማ ቡና ከአበባየው ሀጂሶ ጋር ተለያየ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች ሲዳማ ቡና
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎችቅዱስ ጊዮርጊስየጨዋታ ዘገባኢትዮጵያ መድህን

መድን ከአምስት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

ቴዎድሮስ ታከለ
ቴዎድሮስ ታከለ 1 week ago
Share
SHARE

በሊጉ የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን ቅዱስ ጊዮርጊስን 3ለ0 አሸንፏል።

በጨዋታ የመጀመሪያዎቹ አስር ደቂቃዎች ብልጫውን የወሰዱት መድኖች የፈረሰኞቹ ተከላካይ ብሩክ ታረቀኝ የተሳሳተውን ኳስ ብሩክ ሙሉጌታ ከማይመች ቦታ ላይ ሆኖ ሞክሮ ለጥቂት በወጣችበት ቅፅበት ፈጣን ሙከራን ሰንዝረዋል። በቀጣዮቹ ደቂቃዎች በተሻለ ፈጣን ሽግግር ለመንቀሳቀስ ጥረት ወደ ማድረጉ የገቡት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ሁለት የሚያስቆጩ አጋጣሚዎችን አግኝተዋል። ሀብታሙ ጉልላት ከመስመር ፍፁም ጥላሁን የሰጠውን ኳስ ወደ ጎል ሞክሮ በግብ ዘቡ አቡበከር ኑራ የተመለሰችን ኳስ ፀጋ ከድር ቢያገኛትም በጨዋታው ጥሩ ጊዜን ያሳለፈው አቡበከር አሁንም አክሽፏታል።

በሌላ ሙከራም ከቅጣት ምት ሀብታሙ ነካ አድርጎ የሰጠውን ብርሀኑ አሻሞ አክርሮ መቶ አቡበከር ኑራ ሲተፋት ነፃ ሆኖ ኳስን ያገኘው ሀብታሙ ጉልላት የውጪን መረብ አስነክቶ ኳሷ ወደ ውጪ ወጥታበታለች። ጨዋታዎች ሰላሳዎቹን ደቂቃዎች ሲያጋምስ በድጋሚ ወደ ጨዋታው የገቡት መድኖች ወገኔ ገዛኸኝ አሻምቶ ረመዳን በግንባር ከገጫት ሙከራቸው በኋላ መሪ የሆኑበትን ጎል አስቆጥረዋል። 41ኛው ደቂቃ ላይ ከቀኝ መስመር ረመዳን አሻግሮ ወጣቱ አማካይ ዳዊት በላቸው በደረት አብርዶ የሰጠውን ወገኔ እንድምንም ወደ ቀኝ ላዘነበለው ብሩክ ሙሉጌታ አቀብሎት አጥቂው ሳይቸገር አስቆጥሮታል

ከዕረፍት መልስ በቀጠለው ጨዋታ ጠንከር ያለውን ሙከራ ያስተዋልነው 60ኛው ደቂቃ ላይ ነበር። ከቀኝ መስመር እጅ ውርወራ ተነስታ ከጥሩ ቅብብል በኋላ ፍፁም ጥላሁን ከግራ በኩል ያገኘውን ኳስ አሻምቶ ተገኑ ተሾመ በግንባር ገጭቶ አቡበከር ኑራ በግሩም ቅልጥፍና ኳሷን ከጎልነት ታድጓታል።

- ማሰታውቂያ -

በቀጣዮቹ ደቂቃዎች አንዳች ነገርን ለመፍጠር የተንቀሳቀሱት መድኖች 61ኛው ደቂቃ ላይ ረመዳን የሱፍ ከተከላካይ ጀርባ የጣለውን ኳስ ከጨዋታ ውጪ በሚል የተዘናጉት የቅዱስ ጊዮርጊስ ተከላካዮች አምልጦ ብሩክ ሙሉጌታ ግብ ጠባቂው ፋሩክን አልፎ ለራሱም ለቡድኑ ሁለተኛ ጎል አድርጓታል። 88ኛው ደቂቃ ላይ አሚኑ ነስሩ በሰራው ስህተት ብሩክ በላቸው ያገኛትን ኳስ ፋሩክ ሻኪሉን በማለፍ ተጨማሪ ጎል አክሎ ጨዋታው 3ለ0 መድንን ከአምስት ጨዋታዎች በኋላ ባለ ድል አድርጓል።

You Might Also Like

ሀዋሳ ከተማ ወጣቱን የቀድሞው የግብ ዘቡን አስፈረመ

ወልዋሎዎች አማካዩን የግላቸው አደረጉ

ሀዋሳ ከተማ ሁለገቡን ተጫዋች አስፈረመ

ድሬዳዋ ከተማ ወሳኝ ድል ሲቀናጅ ሀድያ ሆሳዕና እና አዳማ ነጥብ ተጋሩ

ሲዳማ ቡና ከአበባየው ሀጂሶ ጋር ተለያየ

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
Previous Article “ፕሮፌሽናሊዝም ስለሚጎለን ለዛ መማር አለብን” አሰልጣኝ ጢሞቴዎስ ባዬ
Next Article አቤል ያለው እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊለያዩ ነው
Leave a comment

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግወልዋሎወላይታ ድቻዜናዎችየጨዋታ ቅድመ-ዕይታ

የጨዋታ ቅድመ-ዕይታ | ወላይታ ድቻ ከ ወልዋሎ አ.ዮ

ዳዊት ብርሀነ By ዳዊት ብርሀነ 6 years ago
የአምስቱ የኮቪድ 19 ተጠቂ ተጨዋቾች ውጤት ዛሬ ይታወቃል…
አዲስ አዳጊዉ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመስመር አጥቂ አስፈርሟል።
የአ/አ ዳኞችና ታዛቢዎች ማህበር ከ6 አመት በኋላ ዳግም ሊመሰረት ነው
መቻል ሶስት ተጨዋቾች አስፈረመ
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?