“የኢትዮጵያን እግር ኳስ ሚዲያ ላይ የምታወራው ወይንም ደግሞ ቢሮ ቁጭ ብለህ የምታወራው አይደለም”
“የኢትዮጵያን እግር ኳስ በምን በኩል መርዳት እችላለሁ የሚል ጥያቄ ጠይቄ ነው ወደ አሰልጣኝነት የመጣውት”
“የፈለገ ብታወራ ቢጨበጨብልህ ምናምን ሜዳ ላይ እኔና አንተ አይተን መመስከር አለብን”
“ፕሮፌሽናሊዝም ስለሚጎለን ለዛ መማር አለብን”
- ማሰታውቂያ -

“የኔና የስዩም ተቃርኖ የስራ ሳይሆን የአይዲያ ነው”
“የኢትዮጵያን እግር ኳስ ነፃ ያወጣል ብትለኝ በጭራሽ ነው የምልህ ለምን ተረት ተረት ነው” አሰልጣኝ ጢሞቴዎስ ባዬ
የኢትዮጵያን እግር ኳስ ላለፉት አስሬ አምስት አመታት ተመልክቷል። በእነኚህ ሁሉ አመታትም ለውስን ጊዜ በሚዲያው ላይ ከዛም በፋሲል ከነማ ደጋፊነት እና በተጫዋቾች ወኪል ወይም ማኔጀር ሆኖም ሰርቷል። ብዙዎች በማህበራዊ ትስስር ገፁ በሚሰጣቸው እግር ኳሳዊ ትንተናዎች የሚያውቁት እና በአሁኑ ሰዓት በካናዳ ኑሮውን ካደረገ በኋላ በወሰደው የአሰልጣኝነት ስልጠና የስልጠና ማዕከል ከፍቶ ታዳጊዎችን እያሰለጠነ የሚገኘው አሰልጣኝ ጢሞቴዎስ ባዬ ከሰሞኑ ከጋዜጠኛ ሱራፌል አሸናፊ ጋር በነበረው ቆይታ መነጋገሪያ ስለነበረው የአሰልጣን ካሳዬ አራጌ ጉዳይ እንዲሁም ስለ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፣ ስለ ራሱ እና አጠቃላይ ጉዳዮች በሀትሪክ ስፖርት ድረገፅ ከቴዎድሮስ ታከለ ጋር በነበረው ቆይታ ይናገራል።
በቅርቡ ከሰባተኛ ፖድካስት ጋር በነበረህ ቆይታ ስለ አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ የአጨዋወት ፍልስፍና ጋር ሀሳቦችን አንስተህ ነበር ድጋፍም በይበልጥ ደግሞ ነቀፋ አይነት ጉዳዮች ስታስተናግድ ነበር እስቲ ከእርሱ ጉዳይ ብንጀምር ?
“ኮንተንቱን ሰምተህው ከሆነ አንተም በትክክል ፕሮፌሽናሊ ያወራሁት የተጠራው ግለሰብ ስም ብቻም ሳይሆን ማንኛውም ሰው ስለዛ ሰው ሀሳብ ብትጠይቅ የራሴን ኦፒኒየን ከማስቀመጥ ወደኋላ አልልም ያ ሰው ቢቀበለውም ባይቀበለውም ለማንኛውም ግን እግር ኳስ የኦፒኒየን ጉዳዮች ስለሆነ የሚጎረብጠው ሰው ሊኖር ይችላል የሚቀበልህ ሰው ሊኖር ይችላል ብዙም እርሱ አያስጨንቀኝም እውነት ለመናገር ትልቁ ነገር ምንድነው በተሰራው ኮንተንት ላይ በተሰራው ቪዲዮ ላይ ምንድነው ያገኘነው ነው። ሰው በሚያወራበት ሰዓት ምንድነው የተማርነው የሚለውን ይመስለኛል ዋናው ነገር እና ፖዘቲቭ ሰዎች አስተያየት የሰጡ እንደምታየው በውስጥም እየመጡ አስተያየት የሚሰጡኝ አሉ በተቃራኒው ደግሞ የዛ ሰው ሀሳብ ደጋፊ ነኝ የሚሉ ብላይንድሊ ሲቃወሙም ታያለህ ይሄ ኖርማል ጤናማ ነው ብዬ የማምነው ሰዎች ሀሳብ መስጠታቸው ግን ምንድነው መማር አለብን ብዬ አምናለሁ በትክክል አውቀን በትክክልስ ገብቶን ነው ወይ የምንቃወመው ገብቶንስ ነው ወይ የምንደግፈው የሚለውን መጠየቅ ይመስለኛል ዋናው እና የሆነም ሰው ሀሳብ ስትደግፍ በትክክል ተረድተህው ነው ወይ እንደው በደፈናው ነው እንደ አማኞች የምትደግፈው ወይስ ተረድህው ቴዲ የሚያነሳው ሀሳብ በትክክል በደንብ ገብቶህ ነው ወይ የሚለው ይመስለኛል ዋናው ነገር እንጂ የተቃወሙትም የሚደግፉት ምክንያት ካላቸው ኖርማል ነው ብዬ የማስበው ምንም ቢሆን ግን መማር አለብን ብዬ ነው የማምነው ከሁለቱም።”
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ያለበትን ደረጃ መቼስ ጠንቅቀህ ታውቃለህ ብዙ ጊዜ የሚተች እግር ኳስ ነው ያለን ክለቦች አደረጃጀት አልባ ናቸው አስልጣኞች ወጥ የአጨዋወት መንገድ የላቸውም እንደ ሀገርም ስትመጣ ብዙ መሠረታዊ ጥያቄዎችን ታነሳለህ ከዛ ከዛ አንፃር ይህን የጨዋታ መንገድ እንዴት ታያዋለህ ብዙ አጨዋወት በማናይበት ሀገር ይህ መኖሩንስ በአንተ ዕይታ እንዴት ገመገምከው ?
“እንዳልከው ብዙዎቻችን ስለ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ለአመታት ለፍተናል አመታትም ችግሮቹን እናውቃቸዋለን ለይተን ግን መፍትሄ ማምጣት አለብን ነጥቡ ፣ ችግር ሞልቷል የትም ቦታ ስትሄድ ሜዳም ላይ ስትቀመጥ ከጓደኞችህም ጋር ስታወራ እግር ኳስ ውስጥ እስካለህ ድረስ ስለ ችግሩ ነው የምታወራው ብዙ ጊዜ መፍትሔ ማምጣት አለብን ብዬ አስባለሁ ሰውዬውም መፍትሔ አለኝ የኢትዮጵያን እግር ኳስ ማዳን እችላለሁ የሚል ሀሳብ አለኝ የሚል አስተሳሰብ ካለው ይህ ጥሩ ነው እኔ አልቃወምም እንዲህ አይነት ሰዎችን። ትልቁ ነገር ምንድነው የኢትዮጵያን እግር ኳስ ሚዲያ ላይ የምታወራው ወይንም ደግሞ ቢሮ ቁጭ ብለህ የምታወራው አይደለም እግር ኳስ በራሱ እንደዛ የምታወራው አይደለም እንደምታውቀው ተግባራዊ ማድረግ አለብህ ሜዳ ላይ በሜዳ ላይ ተግባራዊ ካላደረክ ምንም አይጠቅምም የፈለገ ብታወራ ቢጨበጨብልህ ምናምን ሜዳ ላይ እኔና አንተ አይነት መመስከር አለብን ብዬ አምናለሁ መመስከር ብቻም ሳይሆን ማሳመን አለብህ በውጤት ተቃዋሚዎች ሁሉ ማመን አለባቸው ሁሉም ማመን አለበት የምታሳምነው ደግሞ በማሸነፍ ነው ግቡ መጨረሻው ውድድር ነው ለዛ ደግሞ ማሸነፍ አለብህ እኔ ግድ የለኝም የካሳዬ ፊሎሶፊ እኔ ግድ የለኝም የቴዲ ፊሎሶፊ ፣ እኔ ግድ የለኝም የጢሞቴዎስ ፊሎሶፊ ትልቁ ነገር ኢትዮጵያ ከምትሰቃይበት የውጤት ቀውስ ማውጣት ይችላል ወይ ነው የኔ ነጥቤ ካላሳየህኝ ለእኔ ተረት ተረት ነው። ስለ እርሱ ሲባል ትሰማለህ በእኔ ግንዛቤ ለፊሎሶፊ የበቃ ነው ብዬ አላስብም ሀሳብ ነው ኳስ ይዘህ መጫወት ነው የትኛው ሰፈር ሀዋሳ ፣ አርባምንጭ ፣ ድሬዳዋ ፣ አዲስአበባ ላይ በየሰፈሩ የምታያቸው አጨዋወቶች ናቸው የተመለከትኩት በየሰፈሩ ሦስት አመት ፖሴሽን ቤዝድ የሆነ እግር ኳስን ነው የሚጫወተው አሪፍ ነው አልቃወምም ይሄን ግን የኢትዮጵያን እግር ኳስ ነፃ ያወጣል ብትለኝ በጭራሽ ነው የምልህ ለምን ተረት ተረት ነው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ነፃ የሚወጣው በብዙ ድምር ውጤት ስለሆነ ማለት ነው። ቴዲ እንደ ጋዜጠኛ ፕሮፌሽናል መሆን አለበት ፣ ጢሞ እንደ አሰልጣኝ ፕሮፌናል መሆን አለበት ክለቦች ፕሮፌሽናሊ መመራት አለባቸው ፣ ፌድሬሽኑ ፕሮፌሽናሊ መከተል አለበት የእነኚህ ድምር ውጤት ነው ኢትዮጵያን ነፃ የሚያወጣት ብዬ ነው የማስበው ሀሳብ ብቻ ነፃ ያወጣታል ብዬ አላስብም እንደውም በይበልጥ ሊደርሺፑ ላይ ብንሰራ ፣ ክለቦች በትክክል እንደ ተቋም ቢቆሙ ተወዳዳሪ የሆኑ ሰዎች መቅረብ ቢችሉ ፣ ከዛ በኋላ ጥሩ ተጫዋቾችን ማብቃት ብንችል ሁሉም ፕሮፌሽናሊ ቢሰራ የዚህ ድምር ውጤት ኢትዮጵያን በአለም መድረክ ያወዳድራታል ብዬ ነው የማምነው እንጂ አንድ የአጨዋወት ሀሳብ ብቻ የኢትዮጵያን እግር ኳስ ይታደጋል ብዬ እምነት የለኝም።”
እስቲ ወደ አንተ ልመለስ ጋዜጠኝነት እንደሞከርክ አውቃለሁ ከዛም ደግሞ የተወለድክበትን አካባቢ ክለብ ፋሲል ከነማን ስትደግፍም አስተውያለሁ በኋላ የተጫዋቾች ወኪል ሆነህ ወደ ዝውውሩም ገብተህ ነበር ከዛ ውጪ ፌስቡክ ላይ የተለያዩ ትንታኔዎችንም ስትሰጥ ትታወቃለህ የኔ ጥያቄ በድንገት ነው ወደ አሰልጣኝነቱ የገባህው ወይንስ ከሀገር መውጣትህ ነው ወደ ስልጠና እንድትገባ ያደረገህ ?
“በጣም አሪፍ ጥያቄ ነው የኔ አመጣጥ አንድ እግር ኳስን እንደሚወድ ሰው ነው የመጣሁት ፣ በትልቅ ደረጃ እግር ኳስ አልተጫወትኩም ማንም አያውቀኝም ፣ በትልቅ ደረጃም ጋዜጠኛም ሆኜ የመጣው ሰውም አይደለሁም። እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ኳስ የምወድ ተራ ሰው ነኝ ከወጣው በኋላ ግን እግር ኳስ ውስጥ ምን መስራት እችላለሁ እግር ኳስ ውስጥ ወደፊት ኬሪዬሬን ማስተካከል እችላለሁ ወይ ምን መስራት አለብኝ የሚል ጥያቄ ጠይቄ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ነው ሞቲቬሽን የሆነኝ ብዬ አምናለሁ። የኢትዮጵያን እግር ኳስ በምን በኩል መርዳት እችላለሁ የሚል ጥያቄ ጠይቄ ነው ወደ አሰልጣኝነት የመጣውት አሰልጣኝ ብሆን የሆነ ቦታ ላይ ማገዝ እችላለሁ ብዬ ውሳኔ ላይ ደርሼ ተምሬ ስልጥኜ ነው እዛም እያሰለጠንኩ ያለሁት እንግዲህ ወደዚህም ያሰብኩት ማለት ነው። የኢትዮጵያ ኳስ ነው በአጠቃላይ ያነሳሳኝ በየዲፓርትመንቱ እግር ኳሱ ብቁ ሰው ያስፈልገዋል የተማረ ሰው ያስፈልገዋል ብዬ ስለማስብ ነው ወደ ኮቺንጉ የመጣሁት በዛ መልኩ ነው ቅድም እንዳልኩህ እግር ኳስ ውስጥ ቴዲ ምን ማገዝ አለበት በሚችለው ራሱን ቀርፆ በሚችለው መቅረብ ስላለበት ለማንኛውም ወደ አሰልጣኝነ የመጣሁት በዛ የተነሳ ነው።”
ከዚህ በፊት ሀገር ውስጥ በነበርክበት ወቅት እንደ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ፣ ስዩም ከበደ እንዲሁም ካሳዬ አራጌን ጨምሮ በማድነቅም ይሁን በትችት በፅሁፍህ ትገልፃቸው ነበር በይበልጥ ግን አድንቀሀቸው የፃፍክባቸው በርከት ይላሉ ላንተ እነኚህ ለየት ያሉ አሰልጣኞች ስለነበሩ ነው በተደጋጋሚ ታደንቃቸው የነበረው ?
“አሪፍ ጥያቄ ነው እንግዲህ የእውቀት ደረጃህ እያደገ ነው የሚሄደው ለምሳሌ እኔ 15 አመት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ነበርኩ በመጀመሪያ የመጀመሪያ 5 አመቶችን እንደ ደጋፊ ነው የምትቆጥረኝ ከዛ ያደገም እውቀት የለኝም ከዛ ግን የተጫዋች ማናጀር ሆኜ ስሰራ በይበልጥ እየተጠጋው ስሄድ ምናምን ስፖርቱን እየተጠጋህ ስትሄድ የምታገኛቸው ነገሮች አሉ በኋላም ደግሞ የመጨረሻዎቹን 5 አመታት ደግሞ አሰልጣኝ ሆነህ የምትሰራቸዉ አሰልጣኝ ሆነህ የምታያቸው ዕይታዎች አሉና በሦስት ስቴጅም ነው የምከፍለው ራሴን ያኛው ዘመን አሰልጣኞች የሚሰሩትን ስታይ እያደነቅ እየተማርክ አንድ በአንድ እያገኘሀቸው እየተማርኩ የመጣሁበት ነበር ሁለተኛው ዘመን አሁን ሦስተኛው ዘመን ላይ ደግሞ አሰልጣኝ ሆነሀል እነሱ ጓደኛ ነው የሚሆኑህ ጓደኛ ስንል የሙያ አጋሮች ከመተቸትም ከመደገፍም ትንሽ ራቅ ትልና እንደ አሰልጣኝ ነው የምትሆነው በዛ መልኩ ነው ለመማር ብዙ ሰዎች ፣ ብዙ ኮቾች አገኝ ነበር ከብዙዎቹ ብዙ ተምሬያለሁ አሁን ግን የስራ አጋሮቼ ባልደረቦቼ ነው የሚሆኑት።”
ሀገር ውስጥ በነበርክበት ጊዜ ከአሰልጣኝ ስዩም ከበደ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት ነበራችሁ ከዛ አልፎ አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ሁሉ አብራችሁ ትታዩ ነበር። በአንዴ ወዳጅ ነበራችሁ ከዛ ደግሞ በተቃራኒው ፌስቡክ ላይ አላስፈላጊ ነገሮችን ሁሉ ትማዘዙ ነበር የስራ አጋጣሚ ወይስ ምን የተለየ ነገር ነበር ያንን ጊዜ ታስታውሳለህ አሁን ላይ ሆነህ ትክክል ነኝ ብለህስ ታስባለህ ?
“በጣም የሚገርምህ የስራ አጋጣሚዎች አልነበሩም እግር ኳሱ እንደምታውቀው በተቃራኒ እኔ እና ቴዲ ልንቆም እንችላለን በተመሳሳይም ልንቆምባቸው የምንችላቸው አጋጣሚዎች ደግሞ ይኖራሉ እግር ኳሱም ስፖርቱም እንደዛ ነው እና የኔና የስዩም ተቃርኖ የስራ ሳይሆን የአይዲያ ነው። አይዲያ ስንል ለምሳሌ ስለ ማኔጅመንት ስናወራ እርሱ ይጠቀመው የነበረው የማኔጅመንት ስኪል ምናምን እኔ በፍፁም የማልቀበለው እና እዛ አካባቢ ካለው ባህል የፋሲል ባህሉ ከማህበረሰቡ ጋር የሚሄድ አልነበረም እና እርሱን እቃወም ነበር በአጠቃላይ ምክንያቱም አካባቢው እንደምታውቀው በይበልጥ አግሬሲቭ ነው ማሸነፍ የሚፈልግ ማህበረሰብ ነው ትንሽ ፐርሰናሊቲ እና ካራክተር የሚፈልግ አሰልጣኝ መሆን አለብህ ከዛ አንግል ትንሽ ዳር እና ዳር ቆመን ነበር በጣም የሚገርምህ እና የሚያስቅህ ግን አሁንም እናወራለን እንደ አሰልጣኝ እንደዋወላለን ሀሳብ እንለዋወጣለን ይሄ ኖርማል ነው ከአይዲያ ግጭት ውጪ አላየሁም።”
ኢትዮጵያ ውስጥ የአሰልጣኝነት ስልጠናን ወስደህ ነበር ወይንስ ካናዳ መሄድህ ብዙ አማራጮች መኖራቸው አስገድዶህ ነው አሰልጣኝ ልትሆን የቻልከው ?
“ካናዳ ውስጥ አንተ ፓሽኑ ካለህ ፍላጎቱ ካለህ ፓዙ ቀጥ ያለ ነው ማንም ሰው ፓሽን ወይም ፍላጎት ካለው ለመማር የሚያስችል መንገድ አለው ይጋብዝሀል አንተ ፍላጎቱ ካለህ በእግር ኳሱ ማለፍ ከፈለክ በደንብ ይጋብዝሀል እና ከዲ ጀምሬ ስልጠናን የወሰድኩት ካናዳ ነው።”
ካናዳ የጀመርከው የአሰልጣኝነት ህይወት ወደ ሀገር ውስጥ የማምጣት ሀሳብ ይኖርህ ይሆን ?
“የትኛውም አለም ላይ ያለ ነው ስልጠና ባርሴሎና ብትሄድ እዚህም ታንዛኒያ ብትሄድ አንድ እኮ ነው (እየሳቀ) ስልጠና ያን ያክል ልዩነት የለውም ትልቁ ምንድነው አዳቭት ማድረግ ካልቸሩን ማወቅ ፣ ተጫዋቾቹን ማወቅ ሌሎች ስቴክ ሆልደሮችም የተለያየ ነገር ስለሚኖራቸው እሱን እሱን ማወቅ ነው እዛም ስሞል ሳይድ ጌም ታገኛለህ እዚህም ኢትዮጵያ የሆነ ሜዳ ላይ ብትሄድ ስሞል ሳይድ ጌም ታገኛለህ ብዙ ልዩነት የለውም ግን እንዳልኩት አዳቭት ማድረግ አለብህ ለምሳሌ አንድ ኢትዮጵያዊ ተጫዋች ኮች ማድረግ እና አንድ ካናዳዊ ተጫዋች ኮች ማድረግ ይለያያል።”
ከእነኚህ ሁሉ አመታት ስለ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ምን ታዘብክ ምንስ አስተዋልክ ምንስ ቢሆን ይሻላል ብለህ ታስባለህ ?
“ፕሮፌሽናሊዝም ማደግ አለበት ብዬ አስባለሁ በጣም አማተር ነን አማተር ከሆንን ደግሞ በዘፈቀደ ነው እግር ኳሱ የሚመራው ማለት ነው። ተጠያቂነት አይኖርም ግልፀኝነት አይኖርም ለምሳሌ ክለቡ ተቋም ካልሆነ ተጠያቂነት ከሌለ ለምንደው ሜዳ ላይ ያሉ ሰዎችን የምትወቅሳቸው ስለዚህ ፕሮፌሽናሊዝምን መከተል አለብን አላየውም ብዙ ይሄንን ፕሮፌሽናሊዝም ስንል በየዘርፉ ያሉ ባለሙያተኞች የተሰጣቸውን ስራ በአግባቡ እና ጥራት ባለው መልኩ መፈፀም እና ማድረግ አለባቸው ፕሮፌሽናሊዝም ስለሚጎለን ለዛ መማር አለብን ለመማር ደግሞ ክፍት ወይም መቀራረብ ፣ ማወቅ ፣ መማር ፣ ማንበብ አለብን ብዬ አስባለሁ።”


