የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
1. እስክንድር ደሳለኝ (ሀዲያ ሆሳዕና) /የቡድን መሪ/ : ክለባቸው ከ ባህርዳር ከተማ ጋር ባደረገው የ20ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 56 ኛ ደቂቃ ላይሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀማቸው በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገዱ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦባቸዋል ።
ስለሆነም የቡድን አመራሩ ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገዱ የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
2. አበበ ጥላሁን (አርባምንጭ ከተማ) : ክለቡ ከ ነገሌ አርሲ ጋር ባደረገው የ2ዐኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 64 ኛ ደቂቃ ላይ ከባድ የአጨዋወት ጥፋት በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ።ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገድ የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
3. ዋሳዋ ጄኦፍሪ (ፋሲል ከነማ): ከታች በተጠቀሱት ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
- ማሰታውቂያ -
- ፋሲል ከነማ-ድሬደዋ ከተማ
- ባህርዳር ከተማ-ፋሲል ከነማ
- ፋሲል ከነማ-ኢትዮ ኤሌትሪክ
- አርባምንጭ ከተማ-ፋሲል ከነማ
- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ-ፋሲል ከነማ
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 15ዐዐ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
4. ሮኅቦት ሰላሎ (ነገሌ አርሲ) : ከታች በተጠቀሱት ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድተመልክቷል ።
- ነገሌ አርሲ-አዳማ ከተማ
- ፋሲል ከነማ-ነገሌ አርሲ
- ነገሌ አርሲ-ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
- ነገሌ አርሲ-ሲዳማ ቡና
- አርባምንጭ ከተማ-ነገሌ አርሲ
ስለሆነም ተጨዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
7. መቐለ 70 እንደርታ ክለቡ ከምድረ ገነት ሽረ ጋር ባደረገው የ20 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የመቐለ 70 እንደርታ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- አብዲ ዋበላ
- አሰጋኸኝ ጴጥሮስ
- ኬኔዲ ገብረጻዲቅ
- መሀመድ ዘጉኤ
- መሀሪ አምሀ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡


