ቤትኪንግ ኘሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት አበይት ጉዳዮች

 

የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ መካሄዱን ከጀመረ አራተኛ የጨዋታ መርሐ ግብር ሲጠናቀቅ አምስተኛው የሊጉ መርሐ ግብሮች ከነገ አንስቶ መካሄዳቸውን የሚቀጥሉ ይሆናል ።

በአራተኛው ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች ላይ በድምሩ አስራ አምስት ጎሎች ከመረብ ላይ ሲያርፉ ከሁለተኛው ሳምንት ጋር ተመሳሳይነት ሲኖረው ከአራቱ ሳምንታት ሲነፃፃር ዝቀተኛው ሆኖ ተገኝቷል ።አዳማ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና ጋር ያደረጉት መርሐ ግብር ብቸኛው ግብ ያልተስተናገደበት የጨዋታ መርሐ ግብር ሆኖ አልፏል ።

 

ሰሆሆ ሜንሳህ ፣ ፍሬው ጌታሁን ፣ ጀማል ጣሰው ፣ ዳንኤል ተሾመ እንዲሁም መሳይ አያኖ በሳምንቱ መረባቸውን ያላስደፈሩ ግብ ጠባቂዎች ሆነው አልፈዋል ።

የፋሲል ከተማው የፊት መስመር አጥቂ ሙጂብ ቃሲም በሳምንቱ ሀትሪክ ሲሰራ ይህም የመጀመሪያው ተጫዋች አድርጎታል ። ሙጂብ ቃሲም በተቋረጠው የውድድር ዓመት ላይም የመጀመሪያውን ሀትሪክ መስራቱ የሚታወስ ነው ።

ጌታነህ ከበደ በተከታታይ ሁለት ጨዋታዎች ሁለት ጎሎችን በማስቆጠር በሊጉ የኮከብ ግብ አግቢነት ላይ ተፎካካሪ ሲሆን ካስቆጠራቸው አራት ጎሎች መካከል ሁለቱ በፍፁም ቅጣት ምት የተገኙ ናቸው ።

በአራቱ ሳምንት የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጉዞ ላይ በድምሩ 69 ጎሎች ከመረብ ማረፍ ችለዋል ።

የአምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከነገ ዓርብ ጀምሮ  እስከ እሁድ እሚከናወኑ ይሆናል። 👇

 

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor