የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ውድድርና አመራር ስነ-ስርዓት ኮሚቴ የአራተኛ ሳምንት የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ መጠናቀቅ ተከትሎ በአራተኛው ሳምንት የሊጉ ጨዋታ የቀረቡለትን ሪፖርቶች አጢኖ በተፈጠሩ ሁነቶች ላይ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል ። የውድድር ስነ-ስርዓት ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ባደረገው ስብስባ የተደረጉ ጨዋታዎችን ጨምሮ ሌሎች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታ ሪፖርቶች መርምሮ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል ።
ከዚህም መካካል የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ከ ባህር ዳር ከተማ ጋር በነበረው ጨዋታ በቅድመ ስብሰባ ወቅት አለመገኘታቸውን ተከትሎ የ 5,000 ብር መቀጮ እንዲከፍል ተወስኖባቸዋል ። ወልቂጤ ከተማ ከዚህ በተጨማሪም የክለቡ ተጫዋች አሲሀሪ አልመሀዲ በቀይ ካርድ መውጣቱን ተከትሎ አራት ጨዋታ እና የ 4,000 ብር ቅጣት እንዲከፍሉ ውሳኔ ተሰጥቷል ።
ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ወላይታ ድቻ ፣ ሀዋሳ ከተማ እንዲሁም ወልቂጤ ከተማ በድጋሚ በተለያዩ ጥፋቶች አምስት እና ከዚያ በላይ ተጫዋቾቻቸው የማስጠንቀቂያ ካርድ መመልከታቸውን ተከትሎ የ 5,000 ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ መወሰኑ ታውቋል ።
በአራተኛው ሳምንት በተደረጉ ጨዋታዎች ሰላሳ ሁለት የማስጠንቀቂያ ካርዶች ሲመዘዙ ግማሽ የሚሆኑት ( አስራ ስድስት ) ከስፖርታዊ ጨዋነት እና አድራጎት ውጪ መሆናቸውን ተከትሎ እንደሆነ ተገልጿል ። ከመጀመሪያው ሳምንት የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አንስቶ አስከ አራተኛው ሳምንት ድረስ 113 የማስጠንቀቂያ ካርዶች በዶኞች ተመዘዋል ።
በተጫዋቾች ደረጃ የፋሲል ከተማው ሱራፌል ዳኛቸው አራት የቢጫ ካርዶችን በማየት ከሊጉ ተጫዋቾች ቀዳሚው መሆኑ በሪፖርቱ ላይ ለመመልከት ተችሏል ።
ሰበታ ከተማ በሊጉ አዲሱ ተስፋዬ በቅዱስ ጊዮርጊሱ ጨዋታ ከተመለከተው የማስጠንቀቂያ ካርድ ውጪ የቢጫ ካርዶችን ቡድኑ ሳይመለከት አራተኛው ሳምንት ላይ ለመድረስ ችለዋል ።
አስተያየት ይስጡ