የጨዋታ ዘገባ | ቡናማዎች ድል ቀንቷቸዋል

 

በአምስተኛ ሳምንት የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡናን ከ ሰበታ ከተማ ሲያገናኝ በቡናማዎቹ ድል አድራጊነት ተጠናቋል ።

በመጀመሪያው አስር ደቂቃ ላይ ኢትዮጵያ ቡና በቀኝ መስመር ላይ በሀይሌ ገብረ ትንሳኤ የመጀመሪያ ሙከራቸውን ሲያደርጉ በግቡ የላይኛው አግዳሚ ላይ ሊወጣባቸው ችሏል ።

ሰበታ ከተማዎች በተቃራኒው በመጀመሪያው አጋማሽ በመልሶ ማጥቃት መጫወትን ሲመርጡ እስራኤል እሸቱ ለ ፍፁም አቀብሎት ተክለማርያም ያዳነበት ሙከራ በቀዳሚነት የሚጠቀሰው ነው ።

በመልሶ ማጥቃት የጨዋታ እንቅስቀሴያቸውን ያደረጉት ሰበታዎች ፍፁም ገ/ማርያም ከጨዋታ ውጪ በመባል ካስቆጠረው ግብ ደቂቃዎች በኋላ ግብ ጠባቂው ፋሲል በረጅሙ ያቀበለውን ኳስ እስራኤል እሸቱ በግሩም ሁነለታ ከመረብ በማሳረፍ ሰበታዎችን ቀዳሚ ማድረግ ችሏል ።

 

ከግቡ መቆጠር በኋላ ተጭነው የተጫወቱት ቡናማዎቹ በቀም መስመር የማጥቃት እንቅስቃሴያቸውን አመዝነው ሲቀጥሉ ሀይሌ አሻግሮለት አቡበከር ሞክሮት የግቡ የጎን መረብ ነክቶ የወጣበት ሙከራ የሚጠቀስ ነው ።

ቡናማዎቹ በጨዋታ ሂደት በመልሶ ማጥቃት ያገኙትን አጋጣሚ ወደ ግብነት ሲቀይሩ ሀብታሙ ታደሰ ወደ ግብነት ሞክሮ ፋሲል የተፋውን ኳስ አቡበከር ናስር ወደ ግብነት በመቀየር ኢትዮጵያ ቡናን አቻ ማድረግ ችሏል ።

በጥሩ የኳስ ቅብብል በተለያዩ አጋጣሚዎች የግብ እድሎችን ለመፍጠር የሞከሩት ቡናማዎቹ የሚያስቆጩ አጋጣሚዎችን በሰበታ ግብ ጠባቂ ፋሲል ገ/ሚካኤል ሊድንባቸወረ ችሏል ። በአንድ ሁለት ቅብብል ያገኛቸውን ኳስ ሀብታሙ ታደሰ በሁለት አጋጣሚዎች ፣ አቡበከር ናስር ከሳጥን ውጪ እንዲሁም ታፈሰ ሰለሞን በግሩም ሁኔታ ሞክሮ ፋሲል ወደ ውጪ ያወጣባቸው ኳሶች የሚያስቆጩ የግብ እድሎች ነበሩ ።

መሪ ያደረገቻቸውን ግብ ካስቆጠሩ በኋላ ወደ ኋላ አፍግፍገው የታዩት እና የተቀዛቀዙት ሰበታ ከተማዎች ከመጀመሪያው አጋማሽ መጠናቀቅ አስቀድሞ በ እስራኤል እሸቱ በመልሶ ማጥቃት ሙከራን ቢያደርጉም በግቡ የላይኛው አግዳሚ ልትወጣ ችላለች ።

በሁለተኛው አጋማሽ ጥቂት ደቂቃዎች ሁለቱም ቡድኖች የተቃዘቀዙ ሲመስሉ ቡናማዎቹ መሪ የሆኑበትን እድል አግኝተዋል ። በቀኝ መስመር ሀብታሙ ታደሰ ከሳጥኑ የቀኝ ጠርዝ ላይ በግሩም ሁኔታ አክርሮ መቶ ቡናማዎቹን መሪ ማድረግ ችሏል ።

ከግቡ መቆጠር በኋላ ዳግም ወደ ግብ መድረስ የቻሉት ኢትዮጵያ ቡናዎች አቡበከር ነስሩ በግራ መስመር የግል ብቃቱን ተጠቅሞ ለሀብታሙ ታደሰ ቢያሻግርለትም ሳይጠቀምበት ቀርቷል ። በእለቱ ድንቅ ብቃቱን ማሳየት የቻለው ታፈሰ ሰለሞን በድንቅ ብቃት ጨርሶ ያቀበለውን ኳስ አቡበከር ናስር ለራሱ ሁለተኛውን ግብ በማስቆጠር የቡናማዎችን መሪነት ወደ ሶስት ከፍ ማድረግ ችሏል ።

በሁለተኛው አጋማሽ ይበልጥኑ የተቀዛቀዙት ሰበታ ከተማዎች የተጫዋች ቅያሪዎችን በማደረግ የማጥቃት አማራጫቸውን ለማስፋት ሲሞክሩ ፍሬ አፍርቶላቸው ቃልኪዳን ዘላለም በቀድሞ ክለቡ ላይ ግብ በማስቆጠር ወደ ጨዋታው እንዲመለሱ ረድቷቸዋል ። ከግቡ መቆጠር በኋላ ሰበታ ከተማዎች ተጭነው ለመጫወት ሲሞክሩ በተለይም ፉአድ ፈረጃ ከሳጥን ውጩ አክርሮ መቶ ግብ ጠባቂው ተክለማርያም ያዳናው የግብ ዕድል የሚያስቆጭ ነበር ።

ጨዋታው በ ኢትዮጵያ ቡና አሸናፊነት ሲጠናቀቅ ድሉን ተከትሎ በመጪው ማክሰኞ የሚካሄደው የሸገር ደርቢ በእግር ኳሱ ቤተሰብ ከወዲሁ በጉጉት እንዲጠበቅ አድርጎታል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor