ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ 25 ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ሰኞ ግንቦት 16 2013 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች) ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል ።

1. ፋሲል ከነማ ክለቡ ከ ሃዋሳ ከተማ ጋር ባደረገው የ 25 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የ ፋሲል ከነማ ቡድን ተጫዋች የሆነጀት ሽመክት ጉግሳ ፣ ሙጂብ ቃሲም ፣ ዓለምብርሀን ይግዛው ፣ ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ እና መጣባቸው ሙሉ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺህ/ እንዲከፍል ወስኗል፡፡

2 ሽመክት ጉግሳ(ፋሲል ከነማ ) በአምስት ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል።

በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 5 አንቀፅ 35 በተቁ 1 (መ) መሰረት 1 ጨዋታ
እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍል ወስኗል።

3 ሐብታሙ ሸዋለም(ወልቂጤ ከተማ) በአምስት ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል።

በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት 1 ጨዋታ
እንዲታገድ እና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍል ወስኗል።

4 ኤልያስ አታሮ(ጅማ አባ ጅፋር ) በአምስት ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል።

በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት 1 ጨዋታ እንዲታገድ እና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍል ወስኗል።

5. አምሳሉ ጥላሁን (ፋሲል ከነማ ) ክለቡ ከሃዋሳ ከተማ ጋር ባደረገው የ25 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ ጨዋታው ካለቀ በኋላ የዕለቱን ዳኞች ለመደብደብ ሙከራ ማድረጉ በዋና ዳኛውና በጨዋታው ታዛቢ ሪፖርት ቀርቦበታል ።

ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት 3 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ/ እንዲከፍል ወስኗል።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor