ጅማ አባጅፋር ነገ ጨዋታቸውን ያደርጉ ይሆን ?

የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ተወዳዳሪ የሆኑት ጅማ አባ ጅፋሮች መውረዳቸውን ካረጋገጡ ሶስት ክለቦች አንደኛው ናቸው ።

የጅማ አባ ጅፋር ተጫዋቾች ላለፉት ሁለት ወራት ደሞዝ አለመከፈላችውን ተከትሎ ልምምድ ካቆሞ ሁለት ቀናት ተቆጥረዋል ።

በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘውን የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብር ተከትሎ የጅማ አባ ጅፋር እግር ኳስ ክለብ ያለፉትን ሁለት ቀናት መደበኛ ልምምዳቸውን አለመስራታቸው ታውቋል ። ተጨዋቾቹ ለክለቡ አመራሮች ደሞዝ እንዲከፈላቸው በተደጋጋሚ ቢጠይቁም ክለቡ መክፈል እንደማይችል ተነግሯቸዋል ።

በ26ኛ ሳምንት የመርሀ ግብሩ የመጨረሻ ጨዋታ ሀዲያ ሆሳዕናን እሚገጥሙት ጅማ አባጅፋሮች የነገውን ጨዋታ የማካሄዳቸው ነገር ጥያቄ ውስጥ ወድቋል።

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team