አርቢትሮች በየጨዋታው እንዲመረመሩ ተወሰነ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሼር ካምፓኒ በድሬዳዋና በሀዋሳ ከተማ የሚደረጉ ጨዋታዎችን የሚመሩ ዳኞች ከጨዋታ በፊት የኮቪድ 19 ምርመራ እንዲያደርጉ ወሰነ።

የካምፓኒው የቦርድ አባላት ወሎ ሰፈር በሚገኘው የፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ባደረጉት ስብሰባ አዲስ አበባ ጅማና ባህርዳር ዳኞቹ አንዴ ተመርምረው ሆቴል ከገቡ በኋላ እንደ ተጨዋቾቹ ከጨዋታው 72 ሰአት በፊት ሳይመረመሩ ቆይተዋል።

ባለፈው ቅዳሜ ለንባብ የበቃችው ሀትሪክ ዳኞቹ ለተጨዋቾቹ የኮቪድ 19 ስጋት ሆነዋል በሚል ዘገባ ከሰራች ከ3 ቀን
በኋላ የካምፓኒው አመራሮች ባደረጉት ውይይት ዳኞቹ በየጨዋታው እንዲመረመሩ ወስነዋል።

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport