ፕሪሚየር ሊጉ በድሬዳዋ የሚካሄድበት ሰዓት ተወስኗል

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቀጣይ አስተናጋጅ ከተማ ድሬዳዋ የውድድሩ ሰአት ጠዋት 3 እና ከቀትር በኋላ 11 እንዲካሄድ ውሳኔ አግኝቷል።

የሊግ ካምፓኒው የቦርድ አባላት ዛሬ ከቀትር በኋላ ባደረጉት ስብሰባ ጠንካራ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ከብዙ ክርክር በኋላ ድሬዳዋ እንድታስተናግድ ቀን ላይ ሙቀቱ ስለማይቻል የጠዋቱ ጨዋታ 3 ሰአት እንዲሆን ተወስኗል። የምሽቱ ግን ዲ ኤስ ቲቪ የሴሪ አ ጨዋታን ጨምሮ የተለያዩ ውድድሮችን ስለሚያስተላልፍ ከቀኑ 11 ሰአት እንዲሆን ተስማምተዋል።

ፓውዛው ለምሽት ጨዋታ ይሆናል ወይ የሚለውን በዶክተር ወገኔ የሚመራው ኮሚቴ ከዲ ኤስ ቲቪ ባለሙያዎች ጋር ቅዳሜ እንዲመለከቱና የመጨረሻ ያሉትን ውሳኔ ሰኞ ለቦርዱ እንዲያቀርቡ የደረሰን መረጃ ያስረዳል።

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport