ኢንተርናሽናል አርቢተር ባምላክ ተሰማ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታን ይመራሉ !

 

ኢንተርናሽናል አርቢተር ባምላክ ተሰማ ከሳምንታት በኋላ በኮሞሮስ ስታድ ዴ ሞሮኒ የሚካሄደውን ተጠባቂ መርሐ ግብር እንደሚመሩ ተገልጿል ።

ሀትሪክ ስፖርት ባገኘችው መረጃ ኢንተርናሽናል አርቢተር ባምላክ ተሰማ ኮሞሮስ ከ ኬንያ የሚያደርጉትን የአራተኛ ዙር የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ እንዲመሩ መመረጣቸው ለማወቅ ተችሏል ።

ከኢንተርናሽናል አርቢተር ባምላክ ተሰማ በተጨማሪ ክንዴ ሙሴ ፣ ተመስገን ሳሙኤል በረዳት ዳኝነት መመረጣቸው ሲታወቅ ለሚ ንጉሴ በአራተኛ ዳኝነት መመደባቸው ይፋ ሆኗል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor