መነሻ ገጽ ዋልያዎቹ በረከት ደስታ በሰርግ ምክንያት ከዋሊያዎቹ ተሰናብቷል
ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

በረከት ደስታ በሰርግ ምክንያት ከዋሊያዎቹ ተሰናብቷል

አጋራ
አጋራ

*በረከት ደስታ በሰርግ ምክንያት ከዋሊያዎቹ ተሰናብቷል

* ፍቃድ አግኝቶ ወጥቶ ባለው ጊዜም አለመመለሱ ከቡድኑ የመቀነሱ ምክንያት ሆኗል

የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከመረጣቸው 36 ተጨዋቾች ሽመልስ በቀለን ጨምሮ ከቀሩት 27 የቡድኑ አባላት መሃል የተጨዋቹ ስም አለበት፡፡

ከ27 ተጨዋቾች 4ቱ የሚቀነሱ በመሆኑ በረከት ከተቀናሾቹ መሃል ይሁን አይሁን የታወቀ ነገር አልነበረም ትልቅ አገራዊ አጀንዳ ላይ የተጠራው ተጨዋቹ ግን ከሰአታት በፊት በደረሰኝ መረጃ በሰርግ ምክንያት ከካፍ አካዳሚ ከሚገኙት ተጨዋቾች ውጪ ሆኗል፡፡

መጀመሪያውኑስ የተቀነሱት ተጨዋቾች ዝርዝር ከመታወቁ በፊት ተናግሮ ቢሆን ኖሮ በሱ ቦታ ከተቀነሱት ተጨዋቾች አንዱ ይቀር ነበር በማለት የበረከትን ድርጊት የስፖርት ቤተሰቡ ተችቷል፡፡ ቡድኑ ህዳር 4 ኒጀርን ገጥሞ የሚመለሰው ህዳር 6 ሲሆን ይህም ቀን የበረከት የሰርጉ ቀን መሆኑ ታውቋል፡፡

ከታማኝ ምንጭ በተገኘ ሌላ የበረከት መረጃ ሰኞ ዕለት ወደ አዳማ ሄዶ ማክሰኞ ምሽት 12 ሰአት ለመመለስ በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ፍቃድ አግኝቶ ከአካዳሚው ከወጣ በኋላ በተባለው ሰአት ባለመመለሱ አሰልጣኙ ደጋግሞ በእጅ ስልኩ ላይ ቢደውልም በረከት ምላሽ አለመስጠቱ አሰልጣኙን አበሳጭቷል፡፡

ተጨዋቹ ዛሬ ጠዋት ሲደውል በአሰልጣኙ መመለስ እንደማይችል መቀነሱ እንደተነገረውና በዚህ የዲሲፕሊን ጥሰትም ከቡድኑ መባረሩ ታውቋል፡፡

ከዚህም በላይ ወጥቶ አድሮ መመለሱ የኮቪድ ምርመራ የግድ በመሆኑም ጭምር በረከት እንዲሰናበት አድርጎታል፡፡ ሰርግ እያለበት እውነቱን አለመናገሩ ምናልባት ኒጀርን አሸንፈው በድል ሲመለሱ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ቀለበቱን ለማድረግ አስቦ ይሆን? የሚሉ ወገኖችም አልጠፉም፡፡

ምናልባት ሲደወልለት ያላነሳው ከ27ቱ ቀሪ ተጨዋቾች መሃል እሆናለሁ የሚል እምነትም ስላልነበረው ይሆናል የሚልም ግምት አለ፡፡ ዋሊያዎቹ በቀናቶች ውስጥ ደግሞ ቀሪዎቹ አንድ ግብ ጠባቂና ሁለት ተጨዋቾች ቀንሰው ጠንካራ ልምምዳቸውን ይቀጥላሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...