በዘንድሮ የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ በመጨረሻ ሳምንት መቆየታቸውን ያረጋገጡት ባህርዳር ከተማወች በዛሬው እለት የሶስት ተጨዋቾች ዝውውር ሲያጠናቅቁ የሶስት ተጨዋቾች ውል ማራዘም ችለዋል ።
በኢትዮ ኤሌክትሪክ ረዥም ጊዜ መቆየት የቻለችው እና በሊጉ ልምድ ካላቸው ግብ ጠባቂ አንዷ ማርታ በቀለ የመጀመሪያ ፈራሚ በመሆን ደርሳለች ።
ሁለተኛው በአርባምንጭ ከተማ በ ተከላካይ ስፍራ በመጫወት መጫወት የቻለችው ማህደር ባዬ ናት ።
ሌላኛዋ በዛሬው እለት መዳረሻዋን በ ጊዮን ንግስቶቹ ቤት ያደረገችው ቤዛዊት ተስፋዬ ናት ቤዛዊት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ መቻል ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና በዘንድሮ ዓመት ደግሞ ሀዋሳ ከተማ መጫወት ችላላች ።
- ማሰታውቂያ -
በተመሳሳይ የሶስት ተጨዋቾች ውላቸውን ማደስ ችለዋል የቡድኑ የመጀመሪያ አንበል ቃልኪዳን ተስፋዬ : አሶሬ አይሶ እና አስቴር ደጋረግ ውላቸውን ማደስ ችለዋል ።



