በዘንድሮ ማራኪ እንቅስቃሴ በሚያስመለክተው በአሰልጣኝ ኤርሚያስ ቡድን ልደታ ክ/ከተማ ጥሩ እንቅስቃሴ ማድረግ የቻለችው ገነት ኤርሚያስ ሁለተኛ ፈራሚ ግብ ጠባቂ በመሆን ባህርዳር ደርሳለች ገነት ሀ-20 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጨምሮ ሀዋሳ ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና አርባምንጭ ከተማ መጫወት ችላለች
በንግስቶቹ ቤት ለመጫወት ፈርማዋን ያኖረችው ሌላኛው ተጨዋች ሳራ ኪዶ ስትሆን ሳራ በሀዋሳ ከተማ እና መቻል በአማካይነት መጫወት ችላለች
ደመቀች ዳልጋ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በድሬዳዋ ከተማ ቆይታዋን ያደረገች ሲሆን የተከላካይ ቦታ ችግራቸውን ለመቅረፍ የግዮን ንግስቶቹን ተቀላቅለች።
በድሬዳዋ ከተማ በአማካይ ቦታ ግልጋሎት ስትሰጥ የነበረችው ማንአየሽ ተስፋዬ መዳረሻውን የጊዮን ንግስቶቹ ጋር አድርጋለች ።
- ማሰታውቂያ -
ወደ ዝውውሩ ጠልቆ በመግባት ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረገ የሚገኘው ቡድኑ የቅድስት ገነነ እና የወርቅነሽ መሠለን ውል ለቀጣይ ዓመት ማራዘም ችሏል ።



