በትላንትናው እለት መገናኛ በሚገኘው በቬልቪው ሆቴል ”ዝክረ ሙሉጌታ ከበደ” በሚል ቃል የተቋቋመው ኮሚቴ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጠ ።
በመግለጫው የ ቀድሞ የ ዋሊያዎቹ አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው እንዲሁም ምክትል አሰልጣኝ የነበረው ስዩም ከበደ እና አቶ ቢልልኝ መቆያ በጋራ በመሆን ኮሚቴው ምን ለመስራት እንዳቀዱ መግለፅ ችለዋል
ከ መግለጫ በፊት ትንሽ ስለ ሙሉጌታ ከበደ ሀትሪክ ልታጋራችው ወደደች !
መሉጌታ ከበደ በደሴ ከተማ ሆጤ ሜዳ በባዶ እግሩ በ 1970 ዓ.ም መጫወት ጀመረ
በመቀጠልም ለቀበሌ :ለከፍተኛ ሀለት:ፔፕሲ እና ለወሎ ምርጥ ቡድን መጫወት ቻለ በተጨማሪም ለ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ለወጣት እንዲሁም ለዋናው ቤሔራዊ ቡድን መጫወት ችሏል
- ማሰታውቂያ -

በቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ቡድን 1977-1989 መጫወት የቻለ ሲሆን ሶስት ጊዜ ኮኮብ ተጨዋች ሶስት ጊዜ ደግሞ ኮኮብ ግብ አስቆጣሪ መሆን ችሏል
እናም ይሄንን የቀድሞ እንቁ ተጨዋች ለመዘከር አብርውት የተጫወቱ ተጫዋቾች ያቋቋሙት ኮሚቴ እንቅስቃሴ የጀመረቱ ከ እቅዳቸው መካከል :- በስሙ ሐውልት :መንገድ ከመንግስት ጋር በመነጋገር ለመሰየም : በስሙ የስፖርት ማዕከል ስታዲየም ለመገንባት አመታዊ የመታሰቢያ ዋንጫ ለማድረግ እንዲሁም ዓመታዊ ሙሉጌታ አዋርድ ለማዘጋጀት በተጨማሪም ፋውዴሽን ለማቋቋም እንደታቀደ ተገልፃል።



