“ውድቀት ሲኖር የትኛውም አመራር ከኔ ጀምሮ ሃላፊነቱን ይወስዳል ያጎደልነው ነገር ካለ ልንጠየቅም ይገባል እንጂ ጅምላ ጭፍጨፋ ተገቢ አይደለም” ሲሉ ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ተናገሩ።
የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ በተመለከተ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በማሪዮት ሆቴል በሰጠው መግለጫ ላይ ፕሬዝዳንቱ ዶክተር አሸብር እንደተናገሩት ” አንድም አትሌት አልመርጥም አንድም አትሌት አልሰርዝም ለምን የትኩረት አቅጣጫ እንደምንሆን አልገባኝም ” ሲሉ አስተባብለዋል።
“ብሄራዊ ቡድን ብሄራዊ አሰልጣኝ ማቋቋም ከብዷል ካምፒኒዎች አሉበት በሌብነት በገንዘብ ላይ የተመሰረተ ነው ጥንቃቄ ይፈልጋል አሁንኮ አሰልጣኞች ባሎች ናቸው ባሎችና ማናጀሮች ከካምፓኒዎች ጋር ሆነው ጠንክረዋል አሁንኮ አሰልጣኝ እየመረጠ ያለው አትሌቱ ነው አትሌቶቹኮ አቅም ገንብተዋል ብሄራዊ ቡድን ለመመለስ በመንግስት ደረጃ ሊሰራ ይገባል” ሲሉ ብሄራዊ ቡድን መልሶ መገንባቱ ከባድ እንደሆነ ተናግረዋል።
ኦሎምፒክ ተሳትፎ ስላሉት ጉዳይ የተጠየቁት ዶክተር
” ኤሊውድ ኪፕቾጌ ያለው ከእኔ ጋር ተመሳሳይ ነው ኬፕቾጌም ሃይሌም አትሌት ናቸው የኦሎምፒኩ ፍልስፍናው ይታወቃል ለተሳትፎ ነው የሮጥነው… ፍልስፍናውን ነው ያወራውት እንጂ ኢትዮጵያ ወርቅ አይገባትም አላልኩም የለፋነውም ለወርቅ ነው አባባሌ በተሳሳተ መንገድ ተተርጉሞብኛል በዚህ አጋጣሚ የተከፋውን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ይቅርታ እጠይቃለው” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
- ማሰታውቂያ -
ከወንድማችን ገዛኧኝ አበራ ጋር በተያያዘ በማለት ስለፈጠሩት አለመግባባት የገለጹት ዶክተር በሰጡት ምላሽ ገዛኧኝ አበራ በመጀመሪያ ጉዞ ላይ ስሙ ነበር ቀረ በ2ኛው ጉዞ በ3ኛው ጉዞ በራሱ ፈቃድ ቀርቶ በአራተኛው በራሱ መጣ እኛን ከህዝብ ጋር ለማወዛገብ መሞከሩ ለአትሌቲክስ አይበጅም ከሱ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝተን የምንተራረም ይሆናል” ሲሉ ዶ/ር አሸብር ተናግረዋል።
ሃላፊነታችሁን ትለቃላችሁ ወይ የተባሉት ዶክተር አሸብር ከእግርኳስ ጋር በተያያዘ ፊፋ ላይ ተከራክሬ አሸንፌ ከዚያ ምሩት ብዬ ለቅቄያለሁ የመጣው ለውጥ የለም በግሌ በጩኧት በሰልፍ ተሸብሬ ሃላፊነቴን አለቅም ሃላፊነታችንን ከለቀቅንም የተናቀው ጠቅላላ ጉባኤ ከወሰነ ብቻ ነው ሰልፍ የዲሞክራሲ መገለጫ ነው እንደ ሃይሌ ሰልፍ ሳይ አልሮጥም በሰልፍ እንደወጣ በሰልፍ ለመግባት ይሞክራል እንደኔ
ህዝብን የሚወክል ጉባኤ መናቅ የለበትም አምባገነንም አይደለንም ህግን አጥብቀን ስለምንሰራ ነው ያልተሸነፍነው ” ሲሉ አስረድተዋል።
በርካታ ሰው ተጉዟል በሚል ለቀረበ ጥያቄ ዶክተር አሸብር በሰጡት ምላሽ ” በርግጥ ድሃ ነን ድህነት ብዙ ያናግራል ከየሴክተሩ ሰውን ልናካትት ሞክረናል ጥቂት የልኡካን ቡድን ይዘው ከሄዱ ሀገራት መሃል እንገኛለን ትንሽ የልኡካን ቡድን ነው ይዘን የተጓዝነው ይህን ማወቅ አለብን ዌብሳይት ፌስቡካችንን በተመለከተ ግን ክፍተት አለብን እንቀበላለን በቀጣይም የሚታረም የሚስተካከል ይሆናል” ሲሉ መልሰዋል።
የርምጃ ውድድር በተመለከተ ትልቁን 6ኛ ደረጃ መጨረሱ ትልቁ ውጤት ዋናውን ጉዳይ ትታችሁ ትንሿን አጉልቶ በመዘገብ ከፍተኛ ሚና የተወጣችሁ ጋዜጠኞች ለተፈጠሩ ችግሮችና ውጤት እንዲጠፋ ከሚፈልጉ ጋር ማበራችሁ ውጤትስ ሲጠፋ የናንተስ ሃላፊነት መሆኑም ዋነኛም ተጠያቂ መሆናችሀን መቀበል አለባችሁ ” በማለት ሀቃቤ ነዋይዋ ኤደን አሸናፊ ቅሬታዋን ገልጻለች።