“አምባገነን ሴረኛና ክፉ ሰዎች ስፖርታችንን በግል ንብረት ልክ እንደ ፒ ኤል ሲ ጠፍረው ይዘው እያሰቃዩት ይገኛሉ” ሲሉ አምባሳደር መስፍን ቸርነት ተናገሩ።
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት ለትሪቩን ስፖርት በላኩት መልዕክት “የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ተሳትፎና የአትሌቲክስ ውጤታማነታችን በአደገኛ ቀውስና የመንገዳገድ ጎዳና ላይ ይገኛል በርግጥ ችግራችን ፈርጀ ብዙ ነው ይህን ለማስተካከል መንግስት ስራዎችን እየሰራ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።
” ድል ለአትሌቶቻችን ይሁን …ለውጤታማነታችን መቀነስ ዋናው ምክንያት ግን የአመራር ተጠያቂነትና የአመራር ችግር ነው” ያሉት አምባሳደር መስፍን ” ከብዙ እልፍ ችግሮች ጋር ከአመት አመት የቀጠልነው ፈተናውን መቅረፍ ባለመቻላችን ነው አሁን ግን መንግሰት ለለውጥ እየተንበሳቀሰ ነው” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።