አሰልጣኝ በረከት ደሙን ያሰናበቱት አዞዎቹ አበባው ቡጣቆን በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ሾመዋል
አርባ ምንጭ ከተማ ክለቡ በውጤት ማጣትና በደካማ አቋም ላይ መገኘቱን ተከትሎ ስር የሰደደ ችግሮችን በማጥራትና በጥልቀት በመገምገም እንዲሁም የማሻሻያ ዕድል በመስጠት ለውጥ ማምጣት ባለመቻሉ በዛሬው ዕለት አስቸኳይ ስብሰባ አድርጓል
በክለቡ የበላይ ጠባቂ እና በክለቡ የቦርድ ሰብሳቢ በእጩነት ከቀረቡና በጊዜያዊነት እንዲያገለግሉ የታጩ የአሰልጣኝ ቡድንን ጨምሮ ሌሎችን የቦርድ አባላትን ተቀብሎ በመወያየት በሙሉ ድምፀ አፅድቋል።
በፀደቀው ውሳኔ መሰረት ፦
- ማሰታውቂያ -
1.አበባው ቡጣቆ የክለቡ ጊዜያዊ አሰልጣኝ
2.ታረቀኝ አርጌቦ የክለቡ ምክትል ጊዜያዊ አሰልጣኝ
3.ሰለሺ ሺፈራው የክለቡ ጊዜያዊ የበረኛ አሰልጣኝ ሆነው እንዲያገለግሉ በመሉ ድምፅ ውሳኔ አፅድቋል።


