ኮትዲቯር ስብስቧን ይፋ አደረገች

ለካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ሀገራት ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ ሁለት ወሳኝ የምድብ ጨዋታቸውን የሚያካሂዱ ሆኗል ።

በዋልያዎቹ ምድብ የምትገኘው ኮትዲቯር ከ ኒጀር እና ከ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ላለባቸው መርሀ ግብር በዛሬው ዕለት በፌዴሬሽኑ ዋና ቢሮ አራት ተጠባባቂ ተጫዋቾችን ጨምሮ ለ ሀያ ስድስት ተጫዋቾች በዋና አሰልጣኛቸው ፓትሪክ ቢምዬል አማካኝነት ጥሪ ቀርቧል ።

ከተጠሩ ተጫዋቾች መካከልም ኒኮላስ ፔፕ ፣ ሰርጂ ኦሪየር ፣ ኤሪክ ቤይሊ ፣ ፍራንክ ኬሲ ፣ አማድ ዲያሎ ፣ ዊልፍሪድ ዘሀ ከተካተቱ ትላልቅ ተጫዋቾች መካከል ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ ።

የኮትዲቯሩ ዋና አሰልጣኝ ፓትሪክ ቢምዬል ለአፍሪካ ዋንጫው ለማለፍ አጥብቂኝ ውስጥ ሲገኙ ለሰላሳ ተጫዋቾች ጥሪ ከማቅረብ ለሀያ ስድስት ተጫዋቾች ብቻ ሲያደርጉ ለአንድም የሀገር ውስጥ ተጫዋች ጥሪ አላቀረቡም ።

ሀትሪክ ስፖርት ባገኘችው መረጃ መሰረት ተለዋጭ ነገሮች በሂደት ከሌሉ በቀር ጨዋታው በቀጥታ በካናል ፕሉስ እና በሀገሪቱ የመገናኛ ቴሌቪዥን RTI 1 እንደሚተላለፍ ለማወቅ ተችሏል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor