ባምላክ ተሰማ ተጠባቂ የካፍ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታን ይመራል

ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል የመሐል ዳኛ ባምላክ ተሰማ ከ ሳምንታት በኋላ የሚካሄደውን ተጠባቂ የአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ በመሐል ዳኝነት እንዲመራ መመረጡ ይፋ ተደርጓል ።

ባምላክ ተሰማ በመጪው መጋቢት 25 በካፍ ሻምፒየንስ ሊግ የሱዳኑ አል ሜሪክ ክለብ ከ ግብፁ ሀያል ክለብ አል አህሊ የሚያደርጉትን ጨዋታ እንዲመራ መመረጡ ለማወቅ ተችሏል ።

ባምላካ ተሰማ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በቀጣይ ሳምንት ከሚካሄዱ የሀገራት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች መካከል ደቡብ አፍሪካ ከ ጋና የሚያደርጉትን ተጠባቂ ፍልሚያ እንዲመራ መመረጡን ወደ እናንተ ማድረሳችን የሚታወስ ነው ።

https://www.hatricksport.net/internewsafrica/

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor