By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: የአ/አ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ :- በከተማው እግርኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የፍትህና የኦዲት ኮሚቴዎች አያስፈልጉም ማለቱ ከፍተኛ ቁጣ ቀሰቀሰ።
Share
Notification Show More
Latest News
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ
ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች
አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ዜናዎች

የአ/አ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ :- በከተማው እግርኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የፍትህና የኦዲት ኮሚቴዎች አያስፈልጉም ማለቱ ከፍተኛ ቁጣ ቀሰቀሰ።

ዮሴፍ ከፈለኝ
ዮሴፍ ከፈለኝ 1 year ago
Share
SHARE

*…. ዋነኞቹ ባለድርሻ የሆኑት ክለቦች ዕጩ ፕሬዝዳንት እንዳያቀርቡ ታግደው ክለብ አልባ ለሆኑት የክፍለ ከተሞች መፈቀዱ ቅሬታ ፈጥሯል…

*…. የጽ/ቤት ሃላፊው ማስጠንቀቂያ ተሰጠው….

የአዲስ አበባ ከተማ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ ስልጣን በሰጠው የደንብ ሰነድ አዘጋጅ ኮሚቴ የስራ ድርሻ ላይ ጣልቃ እየገባ ነው በሚል የአ/አ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ላይ ቅሬታ ቀረበ።

የጠቅላላ ጉባኤው የከተማውን እግርኳስ ዕድገት ላይ ማነቆ በሆኑና በደንቡ ላይ መካተት ያለባቸውን ህጎች አካቶ ለማጸደቅ ጥናት አድርጎ እንዲያቀርብ ስልጣን በሰጠው አካል ላይ ቢሮው ጣልቃ እየገባ አላሰራ ብሏል የሚል ቅሬታ ከተወከለው ኮሚቴ መቅረቡ ተሰምቷል።

- ማሰታውቂያ -

ፌዴሬሽኑ ደንብና የምርጫ ሰኘድ ላይ ካልነበሩትና አጠቃላይ እግር ኳስን በሚመሩ አካላት የማይጠፉ የፍትህ አካላት ፣ የኦዲት ኮሚቴና የይግባኝና ግልግል ኮሚቴ የሌለው መሆኑ እግርኳሱ ላይ ከፍተኛ ሚና ያላቸው የተጨዋቾች ፣ የአሰልጣኞች የዳኞችና ኮሚሽነሮች ማህበራት ድምጽ የሌላቸው መሆኑ ሲያነጋግር የነበረ ክፍተት መሆኑ ይታወቃል። የሰነድና አዘጋጅ ኮሚቴው እነኚህንና የጠቅላላ ጉባኤው የተፈጻሚነት ወሰን የሚለውን በሰነዱ ላይ አካቷል።

ነባሩና በ2013 የጸደቀው ደንብ ከዚህም ውጪ በእግርኳስ ፌዴሬሽኑ ውስጥ በሚካሄዱ የትኞቹም ውድድሮች ላይ የማይወዳደሩት ክፍለ ከተሞች ብቻ ለፕሬዝዳንትነት እጩ እንዲያቀርቡ ዋነኛ ባለድርሻ የሆኑትና ክለቦች ግን ስራ አስፈጻሚ እንጂ ዕጩ ፕሬዝዳንትን እንዳይልኩ የከለከለ ሲሆን በአዲሱ ደንብ ላይ ግን ክለቦች ዕጩ ስራ አስፈጻሚም ሆነ ፕሬዝዳንት እንዲልኩ ተደርጎ የተስተካከለ ቢሆንም ከላይ የተጠቀሱትን አዲሶቹ ደንቦችን ቢሮው በማህበራት ማደራጃ ዳይሬክቶሬት በኩል ከደንቡና መመሪያው ሰርዞ የሰነድ አዘጋጁን ልፋት ገደል ከትቷል በሚል ወቀሳ ቀርቦበታል።

የፍትህና የኦዲት ኮሚቴዎች በጠቅላላ ጉባኤው የሚመረጡና ቀጥተኛ ተጠሪነታቸው ለጠቅላላ ጉባኤው ብቻ እንጂ በፌዴሬሽኑ አመራሮች የማይጠየቁና የማይታዘዙ ዋነኛ ኮሚቴ መሆናቸው እየታወቀ ቢሮው አይሆንም ማለቱ እግር ኳሳዊ አመራር ላይ ያሐውን ክፍተት ያሳያል ተብሏል።

ጉዳዩን የሚከታተሉ ባለሙያዎች ግን የቢሮው ጣልቃ ገብነት ህገወጥ መሆኑን በመግለጽ ጠቅላላ ጉባኤ የወከለውን አካልና የግድ በሰነዱ ሊካተቱ ይገባል የተባሉ አንቀጾችን ሰርዞ መላኩ ከብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ጋር እንዳያጋጨውና የስፖርቱን ዘርፍ የሚመራው አካልና ማህበራት ማደራጃው የእውቀት ማነስ የሚታይበት መሆኑ ቢሮውን ለትዝብት ይዳርጋል እያሉ ስጋታየውን እየገለጹ ነው። የየክፍለ ከተሞቹ ስራ አስፈጻሚውች ይህን ሴራ ያውቁ ይሆን ..? የሚሉት ባለሙያዎቹ በትውውቅና በውስጥ ለውስጥ አሰራር በየክፍለ ከተማዎቹ የሚወከሉ ሰዎች በትክክል አቅም ያላቸው መሆናቸው መረጃው አላቸው ወይ ..? እንዲልኩ የማይፈቀድላቸው ክፍለ ከተሞችስ ለምን ብለው ይጠይቃሉ..? የአሁኑ ምርጫ ላይ ተወካይ የላኩት ከ3 የማይበልጡ መሆናቸውንስ ይረዱት ይሆን ..? ብለው ጠይቀው በየክፍለ ከተማዎቹ ያሉትን ወጣቶችን ለቅሬታ የሚዳርገውን ሂደት እንዲያስቀለብሱ ዋና ስራ አስፈጻሚዎቹን ጠይቀዋል።

ከወራቶች በፊት ከትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር ተያይዞ ከከተማው አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር ውዝግብ ውስጥ የነበሩት ቢሮውና የማህበራት ማደራጃው አሁን ከእግርኳስ ፌዴሬሽኑ ጋር አለመግባባት መፍጠራቸው ልዩነቱ ሌላ አቅጣጫ እንዳይይዝ የብዙዎች ስጋት ሆኗል።

በሌላ በኩል ያለ ፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዕውቅናና ስልጣን ውጪ በራሱ የግል ውሳኔ የፌዴሬሽኑን ጠቅላላ ጉባኤ ግዮን ሆቴል እንዲደረግ ከሆቴሉ ጋር የተነጋገረው የጽ/ቤት ሃላፊው አቶ አበበ ድረስ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው።

የቢሮው ውክልና ያለው የጽ/ቤት ሃላፊው በተደጋጋሚ ጊዜያት የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በማያውቀው ሁኔታ በግሉ እየወሰነ ከስራ አስፈጻሚው የቃል ማስጠንቀቂያ ሲደርሰው እንደነበር ታውቋል። ከሰሞኑ ይህን ድርጊት ቀጥሎበት ጠቅላላ ጉባኤው ህዳር 21 ይደረጋል በማለት ከግዮን ሆቴል ጋር በደብዳቤ ምልልስ ማድረጉ ስራ አስፈጻሚውን ያስቆጣ ሲሆን የጽ/ቤት ሃላፊው ከድርጊቱ እንዲቆጠብ የጀመረውን ግንኙነት እንዲያቆም ያ የማይሆን ከሆነ ለሚደርሰው የህግ ተጠያቂነት ሃላፊነቱ የርሱ መሆኑን በመግለጽ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠው ከታማኝ ምንጭ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

You Might Also Like

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By ዮሴፍ ከፈለኝ
Follow:
Editor at Hatricksport
Previous Article ቢንያም ፍቅሬ የ31 ጊዜ ሻምፒዮኖቹን ተቀላቅሏል
Next Article የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ከፍተኛ አመራሮች ላይ ተጥሎ የነበረው የውጪ ጉዞ ዕገዳ ተነሳ

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
አፍሪካዜናዎች

ኢትዮጵያዊያን ዳኞች ለትልቁ መርሐ ግብር ተመረጡ !

kidus Yoftahe By kidus Yoftahe 5 years ago
የ16ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
የኢትዮጵያ ፉትቦለርስ ኢንተርሚዲየሪ ተመሰረተ !
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለምርጥ 10 ተጫዋቾች ምርጫ 32 ዕጩዎች ታውቀዋል
ዋልያዎቹ በምድቡ የመጀመሪያ ጨዋታ ሽንፈት አስተናግደዋል
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?