በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በተለይም ባለፉት ሁለት አመታት በወላይታ ድቻ አስደናቂ እንቅስቃሴን ማሳየት የቻለው ቢንያም ፍቅሬ ቅዱስ ጊዮርጊስን መቀላቀሉ ተረጋግጧል።
ተጫዋቹ በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ለሚሰለጥነው ቅዱስ ጊዮርጊስ ለሁለት ዓመታት ለመጫወት መስማማቱን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ቢንያም በግብፅ ፕሪሚየር ሊግ ለሚሳተፈው እስማኤልያ ለመፈረም ከቡድኑ ጋር የሙከራ ጊዜ አሳልፎ የነበረ ቢሆንም መዳረሻው የ31 ጊዜ ሻምፒዮኑ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆኗል።
ተጫዋቹ ባሳለፍነው የውድድር ዘመን ለወላይታ ድቻ በ22 የሊጉ ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 8 ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን ባሳየው ጥሩ እንቅስቃሴም ለብሔራዊ ቡድን የመጫወት ዕድል ማግኘቱ ይታወቃል።
- ማሰታውቂያ -
ተስፈኛው ተጫዋች በውድድር ዓመቱ በአማካይ በጨዋታ 1.17 ግቦችን እያስቆጠረ ለሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ የአጥቂ አማራጩን እንደሚያሰፋ ይጠበቃል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ በክረምቱ የዝውውር መስኮት በአጥቂ ቦታ ላይ አብዱ ሳሚዮ እና መሀመድ ኮኔን ማስፈረሙም የሚታወስ ነው።


