መነሻ ገጽ ዜናዎች ዝውውራቸው አጠራጣሪነት የታየበት 9 ተጨዋቾች ለጥያቄ ተጠሩ….
ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

ዝውውራቸው አጠራጣሪነት የታየበት 9 ተጨዋቾች ለጥያቄ ተጠሩ….

አጋራ
አጋራ

ከጸደቀው የክለቦች የክፍያ ስርዓት አስተዳደር መመሪያ  ውጪ የሆነ አሰራርን ተከትሎ ዝውውር ፈጽመዋል በሚል የተጠረጠሩ ዘጠኝ ተጨዋቾች በፋይናንስ አሰራር ተቆጣጣሪ ኮሚቴ ለጥያቄ መጠራታቸው ተሰማ።

ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ እስከ ትላንት ድረስ ከተደረጉና ከጸደቁት ዝውውሮች በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጸድቀው ይፋ ሲደረጉ አልቀበልም ብለው የሄዱት ገንዘብና አሁን በጸደቀው ውል ፈረሙ የተባለበት ገንዘብ በመቶ እና በሁለት መቶ ሺዎች ቀንሶ መሆኑ በርካታ የስፖርት ቤተሰብን ግራ ሲያጋባ ሰንብቷል።

የኡትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽንና የፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ዝምታ ያሳሰባቸው ወገኖችም ቅሬታ ሲያሰሙ ቆይተዋል። አምስት አባላት ያሉት የፋይናንስ አሰራር ተቆጣጣሪ ኮሚቴ ውስጥ ውስጡን እየሰራ መሆኑና ሊግ ካምፓኒው ህገወጦችን እንደማይምር ክለቦችና ተጨዋቾች ከህገወጥ ተግባራቸው
እንዲጠነቀቁ የኮሚቴው ጥርስ የሰላና የማይምር መሆኑን የአክሲዮን ማህበሩ ፕሬዝዳንት መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ ከቀናቶች በፊት ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።

ዛሬ ከቀትር በኋላ በተገኘ መረጃ ከተለያዩ ወገኖች ከቀረቡለት መረጃዎችና የመርማሪው ኮሚቴ ዝውውራቸው አጠራጥሮኛል ያላቸውን ዘጠኝ ተጨዋቾችን ወሎ ሰፈር በሚገኘው የአክሲዮን ሜህበሩ ጽ/ቤት በቀጣዩ ሳምንት መጀመሪያ እንዲገኙ ለጥያቄ መጥራቱ ታውቋል።

የመረጃ ምንጩ የተጨዋቾቹን ማንነት ለጊዜውም ቢሆን ግን ከመግለጽ ተቆጥቧል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...