መነሻ ገጽ ዋልያዎቹ ዋሊያዎቹ በበጎ አድራጎት ተግባር ላይ ተሳተፉ
ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

ዋሊያዎቹ በበጎ አድራጎት ተግባር ላይ ተሳተፉ

አጋራ
አጋራ

👉”ለበጎ አድራጎት ስራና ህብረተሰቡን በቀላሉ ለማግኘት
የዋሊያዊቹ አባላት ቅርብ ናቸው”
አቶ ባህሩ ጥላሁን
/የኢት. እግርኳስ ፌዴሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ/

በመላው ኢትዮጵያ ለሚካሄዱ የበጎ ተግባራት ትልቅ ክብር እንዳለውና ፌዴሬሽኑም ተመሳሳይ የበጎ ተግባራት ክንዋኔ ላይ መገኘቱ ማህበራዊ ሀላፊነትን እንደመወጣት እንደሚያየው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

ካራ የሚገኘው ቦርን አጌን የአእምሮ ጤና ማገገሚያና የፈውስ በጎ አድራጎት ማኅበር የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል ጋር በጋራ በመሆን ትላንት የጎበኙት የፌዴሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን በተለይ ለሀትሪክ ድረገጽ እንደገለጹት
የዋሊያዎቹ አባላት በጉብኝቱ መካተታቸውና በቦታው መገኘታቸው ለማኅበሩ ቀጣይ ጉዞ ትልቅ መነሳሳት እንደሚፈጥርና ተጫዋቾቹ በየሄዱበት ሁሉ አምባሳደር በመሆን የማስተዋወቅ ስራ እንደሚሰሩ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

አቶ ባህሩ እንደገለጹትም ፌዴሬሽኑም በቀጣይ ለበጎ አድራጎት ማህበሩ አቅም በፈቀደ መልኩ የሚያስፈልጉ ነገሮች ሁሉ ለማሟላት እንደሚጥርና ከጎናቸው እንደሚሆን ገልጸዋል ። እንደ ዋና ስራ አስፈጻሚው እምነት ” የአዕምሮ ህመም በየትኛውም ጊዜ በማንናቸውም የሰው ልጅ ላይ ሊከሰት ይችላል ጊዜው ነው የማይታወቀው እንጂ እኛ፣ ቤተሰቦቻችን፣ ጓደኞቻችን፣ የምንወዳቸው ሳይቀሩ እዚህ ሊመጡ ይችላሉና በዚህ መንገድ ማህበረሰቡን የማንቃት ስራ መሰራት አለበት” ሲሉ ገልጸዋል።

አቶ ባህሩ እንዳስረዱት ” ህመሙ እንደማንኛውም ህመም የሚታከም መሆኑን ማስረዳት ይጠበቃል
ስለህመሙ ለህብረተሰቡ ለመግለጽና ለማስረዳት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጨዋቾች ቅርብ ናቸውና እንደ አምባሳደር ይህን በጎ ተግባር በመደገፍ በቀላሉ ለህብረተሰቡ መግለጽ እንደሚችሉ እምነቱ አለኝ ይህን መሰል ችግር ተቋቁሞ ለማለፍ መሰል ተቋማት እንዲበዙና እንዲበረክቱ የበኩላችንን አስተዋጽኦ እንድናደርግ አደራ እላለሁ” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በትላንቱ የማህበሩ ጉብኝቱ ወቅት የማኅበሩ መስራች ፓስተር ኪያ ስብሀት እንደገለጹት “የብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋቾች እኛን በመጎብኘታቸው ትልቅ ደስታ ተሰምቶናል ማህበራችን ሰዎች በአዕምሮ ህመም ምክንያት ጎዳና አይወድቁም በሚል መሪ ቃል እየተንቀሳቀሰ በመሆኑ የብሔራዊ ቡድኑ አባላት የበጎ አድራጎቱ አምባሳደር እንድትሆኑ እጠይቃለሁ በጉብኝታችሁ ደስ ብሎናል ለኛ ዛሬ ትልቅ ቀን ነው” ሲሉ ተናግረዋል። የውዳሴ ዲያግኖስቲክ ባለቤት አቶ ዳዊት ኃይሉ በበኩላቸው በጉብኝቱ እንደተደሰቱ በመግለጽ በቀጣይም ከማኅበሩ ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል። አቶ ዳዊት በጉብኝቱ ወቅትም የምግብ ፍጆታዎች እና የፅዳት እቃዎችን ለማህበሩ ለግሰዋል።

በጉብኝቱ ፍጻሜ መዳረሻም ፌዴሬሽኑ ለበጎ አድራጎት ማህበሩ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ማልያን አበርክቷል። በማኅበሩ የአእምሮ ህሙማን ሆነው ገብተው ያገገሙ አባላት ከውዳሴ ዲያግኖስቲክ ሠራተኞች ጋርም የእግርኳስ ግጥሚያንም አድርገዋል።

ከተመሰረተ ዘጠኝ ዓመት ያስቆጠረው ቦርን አጌን
የአእምሮ ጤና ማገገሚያና የፈዉስ በጎ አድራጎት ማኅበር
120 የአዕምሮ ህሙማንን ከህመማቸው እንዲያገግሙ እየረዳ ሲሆን ወደ 23 የሚጠጉ የህሙማኑ ልጆችን እያስተማረ መሆኑ ታውቋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...