መነሻ ገጽ ዜናዎች የክልል እግርኳስ ፌዴሬሽኖች  የተጨዋቾን ዝውውር እንዳያጸድቁ ተከለከለ
ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየዝውውር ዜናዎች

የክልል እግርኳስ ፌዴሬሽኖች  የተጨዋቾን ዝውውር እንዳያጸድቁ ተከለከለ

አጋራ
አጋራ

“የተጨዋቾች ዝውውር የሚጸድቀው  በፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት በመገኘት ብቻ ይሆናል”
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን

*…..ፋሲል ከነማ በቀድሞ አሰልጣኙ ክስ ከዝውውር መስኮቱ ታግዷል…

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሁለቱም ጾታዎች የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት የፊታችን ሀምሌ 8/2015 እንደሚከፈት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።

ፌዴሬሽኑ ለመጀመሪያ ጊዜ  የሴቶችም ሆነ የወንዶቹ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት  ሀምሌ 8 ተከፍቶ  መስከረም 25/2016 እንደሚዘጋና ዝውውሩ ለ82 ቀናት ክፍት እንደሚሆን አስታውቋል።

ፌዴሬሽኑ በሰጠው ማሳሰቢያ የተጨዋቾች ዝውውር ህጋዊነት የሚጸድቀው በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን
ጽ/ቤት በመገኘት ብቻ እንደሆነ በመግለጽ የክልል የእግርኳስ ፌዴሬሽኖች ዝውውርን ማጽደቅ እንደማይችሉ አስታውቋል። የብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ውሳኔ በተጨዋቾችና በክለቦች መሃል ልዩነት ሲፈጠር ፌዴሬሽኖች ለክለቦቹ ያደላሉ የሚለውን ስሞታ የሚያስቀር ሆኗል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የፋሲል ከነማን ከዝውውር ማገዱን አስታውቋል። የፌዴሬሸኑ የፍትህ አካላት የሆኑት የዲሲፕሊንና የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴዎች በቀድሞ የፋሲል ከነማ  አሰልጣኝ ሃይሉ ነጋሽ / ቲጋና/  እና በክለቡ መሀል የተፈጠረውን የክስ ሂደት ከመረመሩ በኋላ ክለቡ የአሰልጣኙን ቀሪ የ6 ወር ደመወዝ እንዲከፍል የወሰኑትን ውሳኔ ተግባራዊ ባለማድረጉ ሀምሌ 8 ከሚጀመረው የዝውውር መስኮት ተሳታፊነት ማገዱን አስታውቋል።

” አሰልጣኙ  የዲሲፕሊን ኮሚቴ ወስኖ የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ያጸናውን ውሳኔ ክለቡ አልተገበረም  በሚል
ለጽ/ቤቱ ያቀረበውን ጥያቄ በመቀበል ከቀጣዩ የዝውውር መስኮት የታገዳችሁ መሆኑን እንገልጻለን” በማለት  ውሳኔውን ለክለቡ አሳውቋል።

የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ አመራሮች የፍትህ አካላቱ ውሳኔን ካልተቀበሉ ወደ ዓለምአቀፍ የግልግል
ፍ/ቤት የመሄድ የመጨረሻ መብት እንዳላቸው ይታወቃል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...