መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 3ቱም የትግራይ ክልል የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በ2014 የውድድር ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው አሳወቁ።
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

3ቱም የትግራይ ክልል የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በ2014 የውድድር ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው አሳወቁ።

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ግንቦት 24ቀን 2013ዓ.ም ከ3ቱም የትግራይ ክልል የፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ጋር ስለ ቀጣይ የውድድር ዘመን ተሳትፏቸው በተመለከተ ውይይት አደረገ።

በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ አባል እና የማርኬቲንግ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አበበ ገላጋይ እና የኢ.እ.ፌ ዋና ጸሀፊ አቶ ባሕሩ ጥላሁን የተገኙ ሲሆን የመቐለ 70 እንደርታ፣ የወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ ፣ የትግራይ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ የትግራይ ክልል ስፖርት ኮሚሽን አመራሮች በአካል በመገኘት በተጨማሪም የስሁል ሽረ አመራሮች በአካል መገኘት ባለመቻላቸው በቀጥታ የቴሌ ኮንፍረንስ በውይይቱ ላይ ተሳትፈዋል።

በውይይቱ በርካታ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን ክለቦቹ በአሁን ወቅት ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ ያስረዱ ሲሆን አሁን ክለቦቹ ወደ ውድድር ለመመለስ ፍላጎት ቢኖራቸውም ፋይናንስ ትልቅ ማነቆ እንደሚሆንባቸው አስረድተዋል።

ከውይይቱ ያገኟቸውን የሀሳብ ግብዓቶች በመውሰድ ወደ ክለቦቻቸው በመመለስ፣ ከደጋፊዎቻቸው ፣ ከክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ጋር በመነጋገር በአጭር ጊዜ ውስጥ የመጨረሻ ውሳኒያቸውን እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን በኩል ላደረገው 300,000.00( ሶስት መቶ ሺህ ብር) ድጋፍ፣ እንዲሁም በቅርቡ ላደረገው የተጨማሪ የ300,00.00( ሶስት መቶ ሺህ ብር) ድጋፍ በአጠቃላይ ለተደረገው የ600,000.00(ስድስት መቶ ሺህ) ብር ድጋፍ የክልሉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምስጋናውን አቅርቧል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም ክለቦቹ ወደ ውድድር እንዲመለሱ ለማድረግ በሚችለው ሁሉ ለማገዝ ዝግጁ መሆኑን ገለጿል።

Via-EFF

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...