መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ DSTV በድሬዳዋ ጨዋታ የማስተላለፍ ችግር ገጥሞታል
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎች

DSTV በድሬዳዋ ጨዋታ የማስተላለፍ ችግር ገጥሞታል

አጋራ
አጋራ

የቅ.ጊዮርጊስና የሰበታ ይተላለፋል፤የኢት.ቡናና የሀዋሳ ከተማ ጨዋታየመተላለፉ ነገር ገና አልተወሰነም
ጅማና ድሬዳዋ ላይ ቆይታውን አድርጎ ወደ ምስራቃዊቷ የሀገራችን ክፍል ድሬዳዋ የተዟወረው የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስንና ሰበታ ከተማን በ10:00 ሠዓት ኢትዮጵያ ቡናና ሀዋሳ ከተማን በማገናኘት ይጀመራል።

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ያለፉት የ16 ሳምንታት ጨዋታዎች በDSTV ሱፑስፖርት ቫራይቲ የቀጥታ ስርጭት ሽፋን አግኝተው ያለፉ ሲሆን ዛሬ ከሚካሄዱት ሁለት መርሐ ግብሮች አንደኛው የሆነው ምሽት 1:00 ሠዓት ኢትዮጵያ ቡናና ሀዋሳ ከተማን የሚያገናኘው ጨዋታ የመተላለፉ ነገር ጥያቄ ውስጥ መግባቱ እየተሠማ ነው።

ከወደ ድሬዳዋ የመጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከቀኑ በ10:00 ሠዓት የሚካሄደው የቅዱስ ጊዮርጊስን የሰበታ ከተማን ጨዋታ ከቀኑ 10:00 ሠዓት ጀምሮ የቀጥታ ሽፋን የሚያገኝ ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና ከሀዋሳ ከተማ ጋር በቀጥታ በመተላለፉ ዙርያ እስከአሁን ቁርጥ ያለ ነገር አለመሰማቱ ታውቋል።

የሁለቱ ክለቦች የቀጥታ ስርጭት የጨዋታ ሽፋን ያለማግኘቱ ዋናው ምክንያት ከስታዲየም ፓውዛው ደካማነት ችግር ጋር ተያይዞ መሆኑ ታውቋል።
የድሬዳዋ ስታዲየም እንደ አዲስ አበባ ስታዲየም በአራቱም አቅጣጫ ፓውዛ ቢኖረውም የሚሰጠው የብርሃን መጠን በጣም ደካማ፣ጠየሠው ጥላ ደርቦ የሚያሳይ የሱፐር ስፖርት ወይም የቀጥታ የጨዋታ አስተላላፊዎች ያስቀመጡትን የጥራት ደረጃ አሟልቶ አለመገኘት ለተፈጠረው ችግር በምክንያትነት ቀርቧል።

ሊግ ካምፓኒውና የDSTV የቴክኒክ ባለሙያዎች ችግሩን ለመፍታት ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ።
በዚህ በኩል በተለይ በጥላ ፎቅ አካባቢ ከስምንት ያልበለጡ ፓውዛ መብራቶችን የመግጠም ሀሳብ ተነድፎ እንቅስቃሴ እየተደረገ ሲሆን ጥረቱ ስኬታማ የሚሆን ከሆነ ጨዋታው የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ሊያገኝ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።እስከአሁን ይሄ ዘገባ እስከተጠናከረበት ሰዓት የኢትዮጵያ ቡናና የሀዋሳ ከተማ ጨዋታ በመተላለፉ ዙርያ የተወሰነ ነገር ባይኖርም የቅዱስ ጊዮርጊስና የሰበታ ጨዋታ ከተጠናቀቀ በኃላ በሚኖረው የአንድ ሠዓት ክፍተት የመሞከር ሀሳብ መያዙ ታውቋል።

ይሄንን የስታዲየም የመብራት(የፓውዛ) ችግር ለመቅረፍ እንዲረዳ በማሰብ ለድሬዳዋና ለኢትዮጵያ ብ/ቡዶን በመጫወት ያሳለፈው ፉአድ ኢብራሂም ወጪውን በራሱ ሸፍኖ በማምጣት ማስረከቡ የሚታወስ ነው።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...