መነሻ ገጽ ሀዋሳ ከተማ ” ወደ ሀዋሳ የተመለስኩበት ምክንያት በአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት ነው ” ኤፍሬም ዘካርያስ /ሀዋሳ ከተማ/
ሀዋሳ ከተማቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

” ወደ ሀዋሳ የተመለስኩበት ምክንያት በአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት ነው ” ኤፍሬም ዘካርያስ /ሀዋሳ ከተማ/

አጋራ
አጋራ

በትውልድ ከተማው መተሐራ እግር ኳስን የጀመረው የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና ፤ሀዋሳ ከተማ ፤ የአዳማ ከተማ እና የአሁኑ የሀዋሳ ከተማ አማካይ ኤፍሬም ዘካሪያስ ስለ ዘንድሮው የውድድር ፣ ስለ ሀዋሳ ከተማ ፣ ስለ ሙሉጌታ ምህረት እና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ከሀትሪክ ስፖርቱ ፀሀፊ ቅዱስ ዮፍታሔ ጋር ቆይታን አድርጓል።

የሀዋሳ ከተማ የዘንድሮ አቋም . . . . . . .

ጥሩ ነው ብዬ አስባለው አንድ አንድ ጨዋታዎች ላይ እንደ ቡድን ወርደን የቀረንባቸው አጋጣሚዎች ግን ደረጃችንን ወደ ፊት እንዳናሳድግ አድርገውናል ። ከ ሞላ ጎደል አሁን ላይም ቢሆን የምንገኝበት ሁኔታ ጥሩ ሲሆን ወደ ደረጃ ሰንጠረዡ በላይ ለመውጣት የሚያስችል አቅም አለን ።

በቀጣይ ባለን ጊዜ እንደ ቡድን ማስተካከል ያሉብንን ነገሮች ላይ በመስራት ክፍተቶቸቻችንን አስተካክለን በ ባህርዳሩ ውድድር ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን ከዚህ የተሻለ ቡድንን ይዘን እንቀርባለን ።

የቡድናችን ጥሩ ጎን እንደ ቡድን በህብረት መስራታችን ጠንካራው ጎናችን ነው ብዬ አምናለው ፣ ማስተካከል አለብን ብዬ የማስበው ነገር የግብ እድሎችን መፍጠር ላይ መሻሻል እንዳለብን ይሰማኛል ።

የ ዲ ኤስ ቲቪ መምጣት . . . . . . . .

ዲኤስቲቪ መምጣቱ ለሊጋችን በጣም ጥሩ አጋጣሚ ሆኖልናል ፣ ለእያንዳንዳችን ተጫዋቾች የራሳችን ጨዋታ እያየን ክፍተቶቻችንን እንዲሁም ማረም ያሉብንን ነገሮች እንድናርም ይረዱናል ። ከእኛ ከተጫዋቾችን ባለፈም ለስፖርት ቤተሰቡም ቢሆን ጥሩ አጋጣሚ ነው ፣ የተጫዋቾችን ብቃት ለማየት ይረዳቸዋል ። ከዚህ ባለፈ ግን አቅም ላላቸወው ታዳጊ ተጫዋቾች ትልቅ መነሳሳትን ይፈጥርላቸዋል ብዬ አሳብለው ።

ስለ አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት . . . . . . . .

ከ ሙሌ ጋር የመጨረሻዎቹ ኳስ ከማቆሙ በፊት ባሉት ጊዜው አብሮ የመጫወቱን እድል ማግኘት ችዬ ነበር ፣ በዚህም እራሴን በጣም እድለኛ አድርጌ እቆጥረዋለሁ ።

በአሰልጣኝነቱ በጣም ለተጫዋቾች ቅርብ ነው ፣ እንደ ጓደኛም እንደ ታላቅ ወንድምም ነው ለኛ ። ወደ ሀዋሳ ዳግም የተመለስኩበትም ምክንያት በእርሱ ስር ለመስራት ካለኝ ፍላጎት ነው ። የዘንድሮው የውድድር ዓመት በአሰልጣኝነቱ የመጀመሪያው ዓመቱ ቢሆንም ባለነው ልጆች ላይ ለመስራት እያሰበ ያለው ነገር ትልቅ ነው ።

ከ ሀዋሳ ክለብ አመራሮች ትልቅ እገዛን ቢያገኝ ከዚህ በላይ መስራት ይችላል ፣ በቀጣይ አመት ጎበዝ እና ትልቅ አቅም ያለው አሰልጣኝ እንደሚሆን አምናለው ። ለእኛ ለተጫዋቾች ባለው እና በሚሰጠው ክብር ላመሰግነው ስወድ የተሻለ ስኬትን ከወዲሁ እመኝለታለሁ ።

የሀዋሳ ከነማ የቡድን ስብስብ . . . . . . . .

ስብስባችን ከተከላካይ በስተቀር አብዛኞቹ ታዳጊዎች ናቸው ። መሐል ላይ ደግሞ እየተሰለፍን ካለነው እኔ ብቻ ነኝ ልምድ ያለኝ ፣ ስለዚህም ብዙ ስራ መስራት ይጠበቅብኛል ፣ ይሄንን ለማድረግ ደግሞ ብዙ እየጣርኩ እግኛለሁ ።

ታዳጊዎች ስለሆኑ ከጨዋታ ጨዋታ እየተሻሻሉ ነው ፣ ሁሉም በቀጣይ ልምዱን እያገኙ ሲሄዱ ከታዳጊዎች ብዙ እንጠቀማለን ብዬ አስባለው ።

በሁለተኛው ዙር ብዙ ማስተካከያ ጊዜ ስለሚኖረን ያሉብንን ችግሮች ሰርተን አስተካክለን እንመጣለን ። በ አሰልጣኞችም በኩል ቢሆን የሚጨመሩ ተጫዋቾች ለማስተካከል ይሞክራሉ የሚል እምነት አለኝ ። ይህ የማይሆን ከሆነም ባለን ስብስብ ማሰተካከል ያሉብንን ክፍተቶች በመቅረፍ እንቀርባለን ።

ዘንድሮ ሊጉ ከባድ ነው ፣ ሀዋሳ ከነማ ደግሞ ትልቅ ክለብ እና ትልቅ ስም ያለው ክለብ ስለሆነ ያሉትን ችግሮች ለማስተካከል የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን ። ዘንድሮ ፉክክሩ ከበድ ይላል ፣ አሁንም ቢሆን ጊዜው ገና ነው ስለዚህ እያንዳንዱን ጨዋታ በትኩረት የሚጫወት ቡድን ውጤታማ ይሆናል ብዬ አስባለው ።

ስለ ማጥቃት አማራጫቸው ብሩክ በየነ እና መስፍን ታፈሰ . . .

ብሩክ በየነ እና መስፍን ታፈሰ ጎበዝ እና ከዚህ በላይ አቅማቸውን አውጥተው ሀዋሳን ስኬታማ ቡድን ያደርጋሉ ብዬ አስባለው ። አሁንም በማጥቃቱ ረገድ ሙሉ በሙሉ እነሱን ስለምንጠቀም ጎሎችን ከእነርሱ እያገኘን ነው ያለነው ፣ ቢሆንም ግን እነርሱ በሚያገቡት ጎል ብቻ ሀዋሳ አሸናፊ አይሆንም ፣ እንደ ቡድን ያለን ነገር አሸነፊ እያደረገን ይገኛል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...