መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፈረሰኞቹ ዩጋንዳ ኢንቴቤ አየር መንገድ ደርሰዋል
ቅዱስ ጊዮርጊስአፍሪካአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ

ፈረሰኞቹ ዩጋንዳ ኢንቴቤ አየር መንገድ ደርሰዋል

አጋራ
አጋራ

 

በ2018ቱ የቶታል ካፍ ሻምፒዬንስ ሊግ እየተሳተፉ የሚገኙት ፈረሰኞቹ በመጀመሪያው ዙር የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ የሱዳኑን አልሰላም ዋኡ በፎርፌ በማሸነፍ ከዩጋንዳው ካምፓላ ሲቲ (ኬሲሲኤ) ጋር መገናየታቸው ይታወቃል፡፡

ፈረሰኞቹ ተጋጣሚያቸውን ካምፓላ ሲቲ (ኬሲሲኤ) ባለፈው ሳምንት በሜዳቸው አዲስ አበባ ስታዲዬም በገጠሙበት ጨዋታ ያለ ግብ መለያየታቸው የሚታወስ ሲሆን የመልሱን ጨዋታ ለማድረግ ዛሬ ረፋድ 4:05 ከቦሌ አየር መንገድ ወደ ዩጋንዳ ኢንቴቤ አየር መንገድ ያመሩ ሲሆን ከደቂቃዎች በፊት መድረሳቸው ታውቋል፡፡

የፈረሰኞቹ ልዑካን ቡድን ኤንቴቤ አየር መንገድ ሲደርስ በርካታ ዩጋንዳዊያን ለግብ ጠባቂው ሮበርት ኦዶንካራ አቀባበል ከማድረጋቸውም ባሻገር የሬድዮና የቴሌቪዥን ባለሙያዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጓል፡፡

በፈረሰኞቹ ልዑካን ቡድን ስብስብ በጉዳት ምክንያት የፊት መስመሩ ንጉስ ሳላዲን ሰይድ አለመጓዙ ተነግሯል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ፈረሰኞቹ ከኢንቴቤ አየር መንገድ፡ተነስተው ጨዋታው ወደሚደረግበት ወደ ዩጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ እያመሩ ነው፡፡

የዩጋንዳ የቀኑ የአየር ሁኔታ ከፊል ዝናባማ እና ጭጋጋማ መሆኑን የሜትሮሎጂ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡

photo credit-st george page

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ቅዱስ ጊዮርጊስኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

ተጠባቂዉ የአዲስ አበባ ደርቢ በኢትዮጲያ ቡና 2ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

በአቤኔዘር አበበ ተጠባቂው 53ኛው የአዲስ አበባ ደርቢ በኢትዮጵያ ቡና 2–1 አሸናፊነት ተጠናቋል።...

ቅዱስ ጊዮርጊስነጌሌ አርሲዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ እና ሰጎኖቹ ነጥብ ተጋርተዋል

በአቤኔዘር አበበ በመጀመሪያ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ውሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአርሲ ነገሌ ጋር...

ቅዱስ ጊዮርጊስቅድመ ውድድር ዝግጅትዜናዎች

የክለቦች ዝግጅት | ቅዱስ ጊዮርጊስ

የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊው ቅዱስ ጊዮርጊስ የውድድር ዝግጅቱን ምን እንደሚመስል በዚህ...