በዛሬው ዕለት አሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊትን ያሰናበቱት ምዓም አናብስቱ ጊዜያዊ አሰልጣኛቸው ይፋ ሆኗል።
አሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊትን በዛሬው ዕለት ያሰናበቱት መቐለ 70 እንደርታዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስኬት የራቃቸውን እና ባለፈውም አመት የአሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬን መሰናበት ተከትሎ መቐለን ተረክበው የነበሩት አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም በድጋሚ ክለቡን በጊዜያዊ አሰልጣኝነት እንዲመሩ ተሹመዋል።
አሰልጣኝ ፀጋዬ ከትራንስ የጀመረው የስልጠና ህይወታቸው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ሐረር ቢራ ፣ ኢትዮጵያ ቡና ፣ አርባምንጭ ከተማ ፣ ጅማ አባጅፋር እና ወላይታ ድቻን አሰልጥነው አልፈዋል። ባለፈው አመት ከወልዋሎ ስንብታቸው ቀጥሎ መቐለን ያሰለጠኑት አሰልጣኙ በድምሩ በአሰልጣኝነት ሰላሳ አመታትን ቆይተውበታል።



