የሀዲያ ሆሳዕና ተጨዋቾች ከደመወዝና ከጥቅማ ጥቅም ጋር በተያያዘ ትላንት ልምምድ ማቆማቸው ተሰማ።
ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ የ12 ተጨዋቾች ጥቅማ ጥቅም፣ የተጨዋቾቹ የ2 ወር ደመወዝና የአንድ ጨዋታ ኢንሴንቲቭ አልተከፈለንም በሚል ትላንት ልምምድ ማቆማቸው ተሰምቷል።
የቡድኑ አባላት ልምምድ ሲያደርጉ የነበሩት ዝዋይ ሲሆን ክፍያ የማይፈጸም ከሆነ ወደ ድሬዳዋ እንደማያቀኑ ታውቋል።
በጉዳዩ ዙሪያ ምላሻቸውን ለማወቅ ወደ ክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ መላኩ ማዶሮ የግል ስልክ ብንደውልም ስልካቸውን ዝግ በመሆኑ ልናገኛቸው አልቻልንም
አስተያየት ይስጡ