ኮቪድ መጥፎ ጥላውን ያጠላበት የሲዳማ ቡናና የአዳማ ከተማ ጨዋታ ፈተና ውስጥ ወድቋል ከሁለቱም ቡድን ከ31 ተጫዋች በላይ እንደተያዙ እየተነገረ ነው ፎርፌ ይሰጣል?ወይስ ጨዋታው ይተላለፋል?

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ ቀን ውድድር ዛሬ በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ማለትም በ10:00 ሠዓት ባህር ዳር ከተማና ወልቂጤ እንዲሁም በ1:00 ሲዳማ ቡናና አዳማ ከተማ በሚያደርጉት ጨዋታ እንደሚከናወን መርሀ ግብር ቢያዝለትም በተለይ የሲዳማ ቡናና የአዳማ ከተማ ጨዋታ መካሄዱ አጠራጣሪ ሆኗል።

የዚህ ምክንያቱ ደግሞ ከ31 የሚበልጡ ተጫዋቾች የኮቪድ-19 ምልክት ታይቶባቸዋል የሚል የምርመራ ውጤት በመቅረቡ ጨዋታው ጥያቄ ውስጥ እንዲወድቅ አድርጎታል። እንደ መረጃ ምንጮቻችን ከሆነ ሲዳማ ቡና ካለው 32 የቡድኑ አባላት በ27ቱ ላይ የኮቪድ-19 ምልክት እንደተገኘባቸው የምርመራ ውጤቱ የሚገልፅ ሲሆን በአዳማ ከተማ በኩል ደግሞ 21 ተጫዋቾች ላይ በተመሳሳይ ምልክቱ መገኘቱ ነው የተጠቆመው።

የሁለቱም ቡድን አባላትና አመራሮች በተፈጠረው ነገር ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የገቡ ሲሆን በድሬዳዋ ያደረጉትን የምርመራ ውጤት በመጠራጠርና ይሄ ሁሉ ተጫዋች ሊያዝ አይችልም በማለት ትናንት ምሽት በድጋሚ ሀረር ሄደው ምርመራ ማድረጋቸውና ውጤቱን እየተጠባበቁ እንደሆነ ታውቋል። ከሰዓታት በሃላ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት የሁለቱ ክለቦች በሀረር ያደረጉት የሁለተኛ ምርመራቸው ውጤት ለጨዋታ የሶስት ሠዓት እድሜ ሲቀራቸው የሚታወቅ ሲሆን ከዚያ በሃላ በምን አይነት ስነ ልቦና ወደ ሜዳ ገብተው ሊጫወቱ ይችላሉ?የሚለው ከወዲሁ አሰጨናቂ ሆኗል።

ኮቪድ መጥፎ ጥላውን ያጠላበት የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ መጨረሻን ብዙዎች በጉጉት እየጠበቁት ሲሆን ጨዋታው ይተላለፋል? ወይስ ፎርፌ ይሰጣል?ከሁለቱም በርካታ ተጫዋች ተይዞ ፎርፌ የሚሰጠው ለማን ነው? የሚለው ብዙዎች ጆሮአቸውን አቁመው ለመስማት የሚፈልጉት አንኳር ጥያቄ ሆኗል

Hat-trick Weekly Sport Newspaper Founder & Managing Editor.
The First Color Sport Newspaper in the country.

Yishak belay

Hat-trick Weekly Sport Newspaper Founder & Managing Editor. The First Color Sport Newspaper in the country.