መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ “ወልዋሎን ወደ ፕሪምየር ሊጉ በማሳለፋችን፤ ከመቀሌ ከተማም በላይ ሆነን በመቀመጣችን ተደስተናል”አላማንታ (ማሪዮ)
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

“ወልዋሎን ወደ ፕሪምየር ሊጉ በማሳለፋችን፤ ከመቀሌ ከተማም በላይ ሆነን በመቀመጣችን ተደስተናል”አላማንታ (ማሪዮ)

አጋራ
አጋራ

​ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ የኢት 
ዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጪው ዓመት 
ተሳታፊ መሆኑን በትናንትናው ዕለት 
ከመቀሌ ከተማ ጋር ባደረገው የምድቡ 
የመጨረሻ ቀን ጨዋታው ሙሉ ለሙሉ 
ሊያረጋግጥ ችሏል፤ የወልዋሎ አዲግራት 
ዩንቨርሲቲ ክለብ ወደፕሪምየር ሊጉ በቅድ 
ሚያ ለመግባት በመቻሉና በደረጃው ሰን 
ጠረዥም ከተከታዩ መቀሌ ከተማ በላይ 
ሆኖ የምድብ ግጥሚያውንም በማጠናቀቁም 
የቡድኑን ተጨዋቾች እንዳስደሰተም ከክለቡ 
የአማካይ ስፍራ ተጨዋቾች መካከል አንዱ 
የሆነው አላማንታ (ማሪዮ) ለሀትሪክ ስፖርት 
ጋዜጣ አስተያየቱን ሊሰጥ ችሏል፡፡ 
የወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ ክለብ 
ውስጥ ስኬታማ ከሚባሉት ተጨዋቾች 
መካከል በመሀል ሜዳ ላይ የሚጫወተው 
አላማንታ (ማሪዮ) በዘንድሮው የውድድር 
ዘመን የከፍተኛው ሊግ ተሳትፎው ላይ 
ክለቡ በጥሩ ሁኔታ እንዲጓዝና ወደ ፕሪምየር 
ሊግም ለማለፍ እንዲችል የቡድኑ አንድነት፣ 
መፈቃቀር፣ ቡድኑ በወጣቶች መገንባቱ፣ 
አሰልጣኝ ብርሃኔ ገብረእግዚአብኤር እንደ 
አባትና ወንድም ሊመራን መቻሉና የክለቡ 
ከፍተኛ እገዛም ለውጤት እንዳበቃቸውም 
ሀሳቡን አክሎ ገልጿል፡፡ 
የወልዋሎ አዲግራት የመሃል ሜዳው 
ስፍራ ተጨዋች አላማንታ (ማሪዮ) የእግር 
ኳስን መጫወት የጀመረው ተወልዶ ባደገበት 
የኳስ ሜዳ አካባቢ ሲሆን በታዳጊነት እድሜ 
ላይም ለአዲስ አበባ ከተማ፣ ለኒያላ እና 
ለደደቢት ክለቦች በመጫወት እስከ ደደቢት 
የዋናው ቡድን ደረጃም በመዝለቅ ለአጭር 
ጊዜ ቢሆን ሊጫወት ችሏል፡፡ 
የወልዋሎውን የመሃል ሜዳ ተጨዋች 
ክለባቸው ለኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 
ለማለፍ ስለመቻሉ በራሱ የኳስ ሕይወት 
ዙሪያና ሌሎች ጥያቄዎችንም ጠይቀነው 
የሚከተለውን ምላሽ ሰጥቶናል፡፡ 
ሀትሪክ፡- የወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ 
ክለብ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ለማለፍ ችሏል፤ 
በስኬቱ ምን ተሰማህ? የውጤታማነታችሁስ 
ሚስጥር ምን ነበር…

አላማንታ
፡- የወልዋሎ አዲግራት 
ዩንቨርሲተ ክለብ በዘንድሮው የውድድር 
ዘመን ተሳትፎው ባስመዘገበው ስኬታማ 
ውጤት የመጪው ዓመት የሊጉ ተሳታፊ 
መሆኑን በማረጋገጡ በጣም ነው ደስ 
ያለኝ፤ ላገኘነው ተደናቂ የሚባል ውጤትም 
የውጤታማነታችን ሚስጥር የነበረው 
የቡድኑ ተጨዋቾች ላይ የሚታየው የእርስ 
በርስ መዋደድ፣ መፋቀር እና ቡድኑም 
በወጣቶች በመገንባቱም ነው፡፡ ከእዚያ ውጪ 
በሜዳ ላይ እንቅስቃሴያችን ስናጠቃም 
በጣም ጥሩ ነን፤ አስተማማኝ የሆነም 
ግብ ጠባቂ አለን፤ የተከላካይ ክፍላችንም 
አይበገሬነቱን ከጨዋታ ወደጨዋታ በተጓዝን 
ቁጥር እያሳየ በመምጣቱ እና ብዙም ጎል 
እንዳይቆጠርብንም ስላደረገ ያ የስኬታችን 
ዋናው ምንጭ ሊሆን ችሏል፡፡ ሌላው 
አሰልጣኛችን ብርሃኔ ገ/እግዚአብሄርም 
እንደወንድም እና አባትም በመሆን እኛን 
ከማሰልጠን ባሻገር እኛን በመምከርም 
ከፍተኛ አስተዋፅኦን ሊያበረክትልን ችሏል፡
፡ የክለቡም አመራሮች ቡድኑን የቤተሰብ 
ያህልም ይመሩት ስለነበር ያ ከፈጣሪ እርዳታ 
ጋር ታግዞ ጭምር ክለባችንን ለትልቁ 
ውጤት ሊያበቃው ችሏል፡፡
ሀትሪክ፡- የውድድሩ ተሳትፎአችሁ ላይ 
እንደክፍተት የተመለከትከው ነገርስ ነበር?

አላማንታ
፡- የሁለተኛው ዙር ላይ 
አልፎ አልፎ ተደጋጋሚ ግቦችን የምንስትበት 
አጋጣሚ ነበር፤ የአጨራረስ ችግራችን 
ጎድቶን ነበር በኋላ ላይ ግን ልናስተካክለው 
ችለናል፡፡ 

ሀትሪክ
፡- የእግር ኳስ ተጨዋች 
እንድትሆን መነሻ የሆነ አካል ማን ነው?

አላማንታ
፡- የእግር ኳስን እንድጫወት 
የመጀመሪያው መነሻዬ የሆነው ነገር ስሜቴ 
ነው፤ ያለሁበት የኳስ ሜዳ አካባቢ ለአገራችን 
እግር ኳስ በርካታ ተጨዋቾችን ያፈራና ስለ 
ኳስም ቀኑን ሙሉ ቢወራም የማያልቅበት 
ስፍራ ስለሆነ ያ ከፍተኛ ተነሳሽነትን 
ፈጥሮልኝ ወደ ተጨዋችነቱ እንድሳብ 
አድርጎኛል፤ ያም ነው የኳስ መነሻዬም 
የነበረው፡፡ 

ሀትሪክ
፡- የኢትዮጵያ ከፍተኛው ሊግ 
ላይ ለወልዋሎ ምን ያህል ጨዋታዎችን 
አደረግክ… ያለህ ተሳትፎስ ምን ይመስላል?

አላማንታ
፡- የወልዋሎ ዩኒቨርሲቲ 
ክለብን ከደደቢት በመምጣት ከተቀላቀልኩበት 
ጊዜ አንስቶ ያለኝ ቆይታ አበረታች እና ጥሩ 
የሚባል ነው፤ ለቡድኑ በመጀመሪያው ዙር 
15 በሁለተኛው ዙር ላይ 9 የሚደርሱ 
ጨዋታዎችን አድርጌያለሁ፤ ጥሩ 
ለመንቀሳቀስም በቅቻለው፤ ከቡድን ጓደኞቼ 
ጋር በጋራ በመሆንም ክለቡን ለፕሪምየር 
ሊጉ እንዲበቃም የበኩሌን ደርሻ ልወጣም፡፡

ሀትሪክ
፡- ማሪዬ ተብለህ ነው 
የምትጠራው ለምንድነው?

አላማንታ
፡- ማሪዬ የሰፈሬ ልጆች 
ያወጡልኝ ስም ነው፤ በስያሜውም ሊጠሩኝ 
የቻሉት የልጅነት እድሜዬ ላይ አጭር 
ነበርኩና ማሪዬ የሚባል የመጫወቻ አይነት 
ስለነበር ነው ስያሜውን ከቁመቴ ጋር 
በማያያዝ ሊያወጡልኝ የቻሉት፡፡

ሀትሪክ
፡- በኳስ ሜዳ አካባቢ ድሮ ድሮ 
ብዙና በርካታ የእግር ኳስ ተጨዋቾች 
ይፈሩ ነበር፤ አሁን ግን ያ አይታይም ምን 
ይሰማሃል?

አላማንታ
፡- በጣም ያስቆጨኛል፤ 
በጣምም ያሳዝናል፤ ሰፈራችን ያለው ኳስ 
ሜዳው ትምህርት ቤት ተሰርቶበት በመፍረሱ 
እንጂ ብዙ ተጨዋቾችን ማፍራት ይቻል 
ነበር ግን ምን ታደርገዋለህ ያ አልሆነም 
ሁኔታው ትንሽ ስሜትን ይጎዳል፡፡

ሀትሪክ
፡- የእግር ኳሱን ልጅ ሆነህ 
ስትጫወት የቤተሰባችሁ ፍላጎት የቱን ያህል 
ነበር.. መጫወትንስ ይፈቅዱልህ ነበር ወይስ 
ይከለክሉህ ነበር?

አላማንታ
፡- ብዙ ቤተሰቦች የታዳጊነት 
እድሜ ላይ ስትገኝ ኳስን እንድትጫወት 
አይፈቅዱልህም፤ የእኔ ቤተሰቦች ግን በዚህ 
በኩል ተቃራኒ ሆነው ነበር ያገኘኋቸው፤ 
በተለይ አባቴ የእግር ኳስን እንድጫወት 
ከመፈለግ ባሻገር ድጋፍም ያደርግልኝ ነበር 
ያም ነው እኔን አበረታትቶኝ ለዛሬው ደረጃም 
ላይ ለመገኘት የቻልኩት፡፡

ሀትሪክ
፡- የእግር ኳስ ተጨዋቾች 
የታዳጊነት እድሜ ላይ ሲገኙ አንድን ኳስ 
ተጨዋች ሞዴል ወይም ተምሳሌት አድርገው 
ያድጋሉ፤ የአንተስ ሞዴልና የምታደንቀው 
ተጨዋች ማን ነበር?

አላማንታ
፡- የእግር ኳስን ልጅ ሆኜ 
መጫወት ስጀምር የእኔ ተምሳሌትና ሞዴሌ 
የነበሩት ተጨዋቾች በአካባቢያችን ኳስ 
ሜዳ አካባቢ ይጫወቱ የነበሩት የኢትዮጵያ 
ቡናዎቹ ቢኒያም ታዬ ግስላ እና ዮናስ 
ግርማ (ትንሹ ካሳዬ) ናቸው፤ ሁለቱም 
ጥሩ ችሎታው ያላቸው ተጨዋቾች 
ስለነበሩ እነሱን ለማድነቅ እና ሞዴሌም 
ላደርጋቸውም ነው የበቃሁት፡፡

ሀትሪክ
፡- በመጨረሻ…

አላማንታ
፡- በኢትዮጵያ እግር ኳስ 
ውስጥ ወደፊት ትልቅ ተጨዋች መሆንን 
እፈልጋለው፤ በብሄራዊ ቡድን ደረጃና 
ወደ ውጪ ሀገር በመሄድም ለመጫወት 
ያለኝ ፍላጎት ከፍ ያለ ነው፡፡ ስለዚህም 
ልምምዴን ጠንክሬ በመስራት ህልሜን 
ለማሳካት እፈልጋለሁ፡፡ በእዚህ የእስካሁኑ 
ላለኝ የአጭር አመታት የኳስ ጉዞዬም 
ከጎኔ ሆነው ላበረታቱኝ የኳስ ሜዳና 
አካባቢው ጓደኞቼ እንደዚሁም ለቤተሰቦቼ 
እና ላሳለጠኑኝ ሁሉ ምስጋናን ማቅረብም 
እፈልጋለሁ፡፡ 

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

የከፍተኛ ሊግ ውድድር በተለየ ቅርፅ ሊከናወን ነው

የ2019 የኢትዮዽያ ከፍተኛ ሊግ በሀያ ክለቦች መካከል በሁለት ከተሞች ሊከናወን ነው። የኢትዮጵያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግድሬዳዋ ከተማ

አማኑኤል ገብረሚካኤል ድሬዳዋ ከተማን ተቀላቀለ

አማኑኤል ገብረሚካኤል በይፋ ለከፍተኛ ሊጉ ድሬዳዋ ከተማ ለአንድ አመት ፈርሟል። በመቐለ 70...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግየዝውውር ዜናዎች

ከፍተኛ ሊግ | ድሬዳዋ ከተማ ሰባት ተጫዋቾችን አስፈረመ

ከፕሪምየር ሊጉ ከአመታት ቆይታ በኋላ የወረደው እና በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ2019 የውድድር...