አሁንም እንደ በፊቱ ቀጠሮ ላይ ቀልድ አናውቅም ከተባሉ ያለጥርጥር አባባሉ የሃትሪክ ነው…
ለምንወዳቸው አንባቢዎቻችን እውነተኛ አክብሮት አለን አድናቆት ለተሞላው አስተያየቶቻችሁና ለሚያርመን ግሳጼያችሁ ጆሮና ልባችን ክፍት ሆኖ ቆይቷል። ግንኙነታችንም እንዲህ ግልጽ ሆኖ እንደሚቀጥልም እርግጠኞች ነን።
እንዳልነው ነገ ጠዋት በቀጠሮው ሰአት እንገኛለን…..በመረጃዎቻችን ዘና ለማለትም ሆነ ቁም ነገር ለመቅሰም ምርጫዎ ያድርጉን አናሳፍሮትም..
*… በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ደረጃ የወንዶችን የቻን የአፍሪካ ዋንጫን ለመምራት የተመረጠችው ብቸኛዋ እንስት አርቢትር ሊዲያ ታፈሰ ብቃቷን አሳይታ የወከለችውን ህዝብ አኩርታ ተመልሳለች ክብር ሰጥቶ የተቀበላት ያመሰገናት አንድም የስፖርት አመራር አለመኖሩ ግን አስከፍቷታል..መቼ ነው ግን ጀግኖቻችንን በተገቢው መንገድ የምናከብረው? አርቢትሯ የሚሰማትን ለሃትሪክ ተንፍሳለች…
- ማሰታውቂያ -
*… በኮቪድ 19 የማገገሚያ ክፍል ውስጥ ለተኛ ሰው ማስጠንቀቂያ መላክ ምን ይሉታል?የጅማ አባጅፋሩ ትርታዬ ደመቀ “የማገገሚያ ክፍል ውስጥ ተኝቼ በክለቡ አመራሮች አቋምህን አስተካክል የሚል ደብዳቤ ተሰጥቶኝ ሞራሌ ተነክቷል” ሲል ለፌዴሬሽኑ ከሷል…. ከሃትሪክ ጋርም ቆይታ አድርጓል…
*… ተሰናባቹ ከ14 አመት ፕሬዝዳንትነት በኋላ ራሳቸውን ያገለሉት የሲዳማ ቡና ፕሬዝዳንት
አቶ መንግስቱ ሳሳሞ ” ሲዳማ ቡና ካሸነፈ
ቡድኑ የሲዳማ ህዝብ ነው ከተሸነፈ ግን የመንግስቱ ነው”በማለት ስንብታቸውን ተከትሎ የተሰማቸውን ለሃትሪክ ተናግረዋል…
*… ተሰናባቹ የድሬዳዋ ከተማ አሰልጣኝ ፍሰሃ
ጥዑመልሳን “ለቀጣዮቹ ሁለት ጨዋታዎች ቢታገሱኝ ደስ ይለኝ ነበር በቀጣይ የማገኛቸውን ሀዋሳና ሰበታን አሽንፌ 6ኛ ደረጃ ላይ ቡድኑን አመጣው ነበር….መጪው አሰልጣኝ ሁለቱን ክለቦች ቢረታ ይኸው ቡድኑን ከጉድ አወጣው ሊባል ነው ወይ?” ሲል ለሃትሪክ አስተያየቱን ሰጥቷል….
ከውጪ ደግሞ፦
*….በሻምፒየንስ ሊጉ ጥሎማለፍ ባርሴሎና
ከፒ ኤስ ጂ ጋር የሚያደርጉትን ጠንካራ ፍልሚያ ጨምሮ በሻምፒየንስ ሊግ ማክሰኞና ረቡዕ ምሽት ጨዋታዎች አዳዲስ መረጃዎች ተጠናክረዋል ….
*… የማን.ዩናይትዶቹ የፊት መስመር ተዋጊዎች ማርሲያልና ራሽፎርድ ካደረጓቸው 250 ጨዋታዎች በኋላ ማን የተሻለ ነው የሚል ምርጥ ንጽጽር ተካቶበታል..
*…በዩሮፓ ሊግ የፊታችን ሃሙስ ምሽት ስለ ሚጠበቀው የቤኔፊካና አርሰናል ፍጥጫም ሃትሪክ ያዘጋጀችው ዘገባም አለ….
ነገ ጠዋት ሀትሪክ እጅዎ ስትገባ ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎች አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ያገኛሉ የርስዎ የሆነችውን ሀትሪክን በእጅዎ ቢያስገቡ ይጠቀማሉ ይዝናናሉ
……ቅዳሜና እሁድዎ የተባረከ ይሁን…….
https://www.Hatricksport.net