” በደሞዝ ከውጭ ሀገር ግብ ጠባቂ በማነሴ የመጫወት እድል ተነፍጎኛል ” ምንተስኖት አሎ /ሰበታ ከተማ/

 

በፕርሚየር ሊጉ የተለያዩ ክለቦች በመጫወት ብቃቱን በማሳየት ሀገራችን ኢትዮጵያ ግዙፏን ኮትዲቯር በረመረመችበት ጨዋታ ጨምሮ በተለያዩ ጊዜያት የሀገሩን ስም ካስጠሩ ግብ ጠባቂዎች መካከል ነው ።

የዘንድሮውን የውድድር አመት በቀድሞው የ ዋልያዎቹ ዋና አሰልጣኝ ኢንትራክተር አብርሀም መብርሀቱ በሚመራው ሰበታ ከተማ እያሳለ ይገኛል ። ከዚህ ቀደም በ ስሑል ሽረ ፣ መከላከያ ፣ ባህርዳር ከተማ ከ ሀገር ውስጥ አልፎም በአውሮፓዊቷ ምድር ቱርክ ጥሩ የሙከራን ጊዜ አሳልፎ በ ኮሮና ቫይረስ ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰው ምንተስኖት አሎ ከሀትሪክ ስፖርት ፀሀፊ ቅዱስ ዮፍታሔ ጋር ቆይታን አድርጓል ።

ሊጉ ወደ ሀገሩ ውስጥ ግብ ጠባቂ ማዞሩን እና አጋጣሚዎቹን . . . . . . .

“ሊጋችን ወደ ሀገር ውስጥ ግብ ጠባቂዎች ፊቱን ማዞሩን እንደ መልካም አጋጣሚ ነው የምወስደው ምክንያቱም ብዙ አቅም ያላቸው የሀገር ውስጥ ግብ ጠባቂዎች አሉ ፣ ነገር ግን ከውጪ በሚመጡ ግብ ጠባቂዎች ተሸፍነው ይቀራሉ ፣ ለአብነት ያክል እኔ ላይ ከዚህ ቀደም የደረሰውን ማንሳት ይቻላል ።

ብዙም ባይባል አንድ አመት የውጪ ግብ ጠባቂ ያለበት ክለብ ውስጥ ተጫውቼ ማለፍ ችያለው ። በምጫወትበት ጊዜም ያን ያህል ባይሆንም ጥሩ ፉክክር ነበርን እና ከግማሽ በላይ ጨዋታዎችን መጫወት ችያለው ፣ ከዚህ ባለፈም ጥሩ ትምህርት የቀሰምኩበት አጋጣሚም ነበር ።

እንደ ጥሩ አጋጣሚ የማልወስደው ፈተና ገጥሞኝ ያውቃል ፣ የውጭ ግብ ጠባቂ የነበረበት ክለብ በምጫወትበት ወቅት ብዙ ጨዋታዎችን የመጀመሪያ ተሰላፊ ሆኜ ተጫውቻለው ፣ ነገር ግን ከመጀመሪያ ቋሚ ተሰላፊነት የወጣሁባቸው ምክንያት በጣም ያዘንኩባቸው አጋጣሚ ነበር ።

በተለይም ከውጭ ሀገር መጥቶ በክለቡ የነበረው ግብ ጠባቂ ደሞዙ ከእኔ አንድ እጥፍ ይከፈለው ስለነበረ እሱ ያንን ደሞዝ እየተከፈለው ተጠባባቂ ወንበር ላይ ለምን ይሆናል በሚል ብቻ የጨዋታ ጊዜ ተነፍጌ የቆየሁበት ወቅት ለእኔ ከባዱ ጊዜ ነበር ።

ይህ ውሳኔ ለሁሉም የሀገር ውስጥ ግብ ጠባቂዎች ጥሩ አጋጣሚ ነው ሆኖም ግን እኛም አቅም እንዳለን ለማሳየት በርትተን መስራት ይጠበቅብናል ።”

ስለ ኢንስትራክተር አብርሀም እና ስለግል ብቃቱ

በልምምድ ወቅት የሚሰጡኝን ልምምዶች በአግባቡ እሰራለው ፣ ከዚህ በተጨማሪም በግል ልምምዶችን እሰራለው ። ይሄም በጨዋታ ወቅት ጥሩ ነገሮችን በሜዳ ላይ እንዳሳይ እየረዳኝ ይገኛል ።

ለእኔ በ ኢንስትራክተር አብርሀም መብርሀቱ ስር መስረት ዳግም ለመስራት መቻሌ ጥሩ አጋጣሚ ነው ። ምክንያቱም ኢንስትራክተር አብርሀም መብርሀቱ ትልቅ አሰልጣኝ ነው ፣ ከእርሱ ጋር በመስራቴ በጣም ደስተኛ ነኝ ። ከዚህ በተጨማሪም ያለኝን አቅም እንዳሳድግ ብዙ ነገሮችን እየረዳኝ ይገኛል ።”

ስለ ሰበታ እና ዳኝነት ጉዳዮች. . . . . .

“ክለባችን ላይ በተደጋጋሚ ጨዋታ ላይ የዳኝነት ስህተቶች ይስተዋላሉ ። ይህም ሁነት አሁን ላለንበት ደረጃ አድርሶናል ብዬ አስባለው ። በዳኝነት ስህተት ብዙ ነጥቦችን አጥተናል ዋጋም አስከፍሎናል ።

ሆኖም ግን የባህርዳሩ ውድድር ላይ የተሻለ ነገር እንደምሰራ እና የተሻለ ውጤት በማምጣት ደረጃችንን ከፍ አድርገን እንደምንጨርስ ከፈጣሪ ጋር አምናለው ።”

ስለ ክለቡ ጠንካራ የግብ ጠባቂ ስብስብ . . . …

“እውነት ነው ክለባችን ላይ ሶስት ጥሩ አቅም ያላቸው ግብ ጠባቂዎች አሉን ፣ ያለንበትም እድሜ ተመሳሳይ እንደመሆኑ ሜዳ ውስጥም ከ ሜዳ ውጪም ጥሩ መተሳሰብ በመካከላችን ይገኛል ። ሌላው ነገር ደግሞ እድሉን በምናገኝበት ሰዓት የተሻለ” አቅማችንን አውጥተን ለመጫወት ጥሩ ፉክክር እናደርጋለን ።

ከወራጅነት ጋር ስለሚነሱ ጉዳዮች . . . . . . .

ብዙ ነገር ይወራል ነገር ግን እኛ በዚህ ሰዓት ስለ መውረድ ሳይሆን የምናስበው ከመሪዎቹ ጋር በሊጉ ጥሩ ተፎካካሪ ሆነን ስለ መጨረስ ነው ፣ ጥሩ ተፎካካሪም እንደምንሆን ባለ ሙሉ ተስፋ ነኝ ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor