በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 29ኛ ሳምንት በተከታታይ በሜዳ እና፡በሌሎች ችግሮች ሲንከባለል ለሶስተኛ ቀን፡የደረሰው የሱሉልታ እና መቐለ ከተማ ጨወታ ዛሬ 5ሰዓት ላይ፡በአዲስ አበባ እስታዲየም የተካሄደ ሲሆን የጨዋታው የመጀመሪያው አጋማሽ ብዙ ሳቢ ባለሆነ መልኩ ነበር የተጠናቀቀው፡፡
በሁለተኛው አጋማሽ ጨዋታዉ እንደ ተጀመረ ሱሉልታ ከተማ የመጀመሪያውን ጎል ሲያስተናግዱ ፡፡ በዙም ሳይቆይ በ66ኛ ደቂቃ የጨዋታው አርቢትር ለመቀለ ከተማ የፍፁም ቅጣት ምት ሲሰጡ የሱሉልታ ተጨዋቾች የተሰጠው ፍፁም ቅጣት ምት ተገቢ አይደለም በማለት ተቃውሞ በማሰማት ሜዳውን ለቀው ሊወጡ ችለዋል በዚህም የሱሉልታ ተጨዋቾች በደጋፊዎቻቸው ወደሜዳ እዳትመለሱ በሚሉ ድምጾች ጫና ውስጥ ሲገቡ ለመታዘብ ተችሏል፡፡
ከ25ደቂቃዎች በኃላ የጨዋታው አርቢተር ጨዋታው መቋረጡን አውጀዋል፡፡
የአሰልጣኞች አስተያየት
- ማሰታውቂያ -
ዳዊት ፀኃዬ(መቐለ ከተማ)
ጨዋታው በመረሀ ግብሩ መሠረት አልተካሄደም ፡፡ሱሉልታዎች ይሄን ጨዋታ ለማድረግ ተቸግረዋል ቢይንስ ሶስት ግዜ ወደ ሜዳቸው ተመላልሰናል፡፡ ለአንድ ጨዋታ ከአዲስአበባ ሱልልታ ድረስ ሶስት ጊዜ ተመላልሰናል፡፡ ይሄን ጨዋታ ለማድረግ በብዙ ጫናዎች ውስጥ ማለፍ ነበረብን፡፡ለዚህ ሁሉ የኛ ጫና ውስጥ መግባት የፌዴሬሽኑ ጠንካራ የአመራር ውሳኔ አለመታየቱ ነው፡፡እስከ 66ኛ ደቂቃ የተቋረጠበት ደቂቃ ደረስ እየመራን ነበር፡፡ማሸነፍ መሸነፈ ያለ ነው ሱልልታዎች የኛን አሸናፊነት መቀበል አለባቸው፡፡ደኛው የሰጠን የፍፁም ቅጣት ምት ተገቢ ነው፡፡
ታደሰ ጥላሁን (ሱልልታ ከተማ)
ዳኝነቱ በተወሰነ መልኩ ፍትሀዊ አይደለም እላለሁ፡፡ ሁለተኛ አጋማሽ ላይ የተሰጠብን ፍፁም ቅጣት ምት ተገቢ አይደለም አያሰጥም እላለሁ ፡፡ለዛም ነው በደጋፊዎቻችን እና በተጫዋቾቻችን ላይ ቅሬታ ያሳደረው ፡፡ ተጫዋቾቼ ተመልሰው ገብተው ጨዋታውን እንዲያደርጉ ለማግባባት ከፍተኛ ጥረት አድርጊያለሁ ሆኖም ተጨዋቾች ከደጋፊዎች ጋር አለመግባባት በመፍጠራቸው ጨዋታውን መልስን ለመቀጠል ሳንችል ጨዋታው ሊቋረጥ ችሏል፡፡