መነሻ ገጽ ዜናዎች የከፍተኛ ሊግ ወድድር የኦንላይን ቀጥታ ስርጭት ሲያገኝ የተሳታፊ ቁጥርን በሒደት ለመቀነስም ውሳኔ ተላልፏል
ዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

የከፍተኛ ሊግ ወድድር የኦንላይን ቀጥታ ስርጭት ሲያገኝ የተሳታፊ ቁጥርን በሒደት ለመቀነስም ውሳኔ ተላልፏል

አጋራ
አጋራ

የከፍተኛ ሊግ ወድድር የኦንላይን ቀጥታ ስርጭት ሲያገኝ የተሳታፊ ቁጥርን በሒደት ለመቀነስም ውሳኔ ተላልፏል

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ጥራትን ከፍ ለማድረግ በዘንድሮው የውድድር ዓመት በርካታ ስራዎች እንደሚሰሩ ዛሬ በአፍሮዳይት ሆቴል ከሊጉ ክለቦች ጋር በተካሄደው የምክክር መድረክ ላይ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከFIFA ጋር በመነጋገር በፊፋ ፕላስ ፕሮጀክት በኩል ውድድሩ የቀጥታ የኦንላይን ስርጭት እንዲያገኝ ስምምነት የተደረሰ ሲሆን ይህም የውድድሩን ደረጃ ከፍ ለማድረግ አይነተኛ አስተዋፅዖ እንደሚኖረው ተገልጿል። በዛሬው የምክክር መድረክ ላይም ከኦንላይን ስርጭቱ ዘላቂ ጥቅም ለማግኘት የውድድሩን ጥራት መጨመር አስፈላጊ መሆኑ መግባባት ላይ የተደረሰበት ሲሆን የከፍተኛ ሊግ ውድድር ኮሚቴ የተሳታፊ ክለቦችን ቁጥር በየዓመቱ በሒደት በመቀነስ ሊጉን ለማስተዳደር አመቺ በሆነ እና ወደ ገበያ እድልነት በሚቀይር መልኩ ጥራቱን ከፍ ለማድረግ ከውሳኔ መድረሱ ተገልጿል።

በዚህም መሠረት የ2015 የውድድር ዓመት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተፈጠረው የፀጥታ ችግር መሳተፍ ያልቻሉ ክለቦችን ጨምሮ 42 ክለቦች በሦስት ምድቦች ተወዳዳሪ የሚሆኑ ሲሆን በየምድቡ 14 ክለቦች ተሳታፊ በማድረግ በዓመቱ መጨረሻ ከየምድቡ የመጨረሻ 5 ደረጃዎች ይዘው የሚያጠናቀቁ በአጠቃላይ 15 ክለቦች ወደ አንደኛ ሊግ እንዲወርዱ ተደርጎ ከአንደኛ ሊግ ደግሞ ለ2016 የውድድር ዘመን 4 ክለቦች ወደ ከፍተኛ ሊግ እንዲያድጉ ተወስኗል። ይህም በ2016 የሚሳተፉ ክለቦችን ቁጥር በመቀነስ ሦስት የነበረውን ምድብ ወደ ሁለት ዝቅ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

via : EFF

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሽንፈት ሲገጥመው በድንጉዛ ደርቢ የጦና ንቦቹ እና ኤሌክትሪክ ድል ቀንቷቸዋል

በሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ተከታታይ ሽንፈትን በሸገር ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንፊፋ

ፊፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ጥሎት የነበረውን የዝውውር ዕገዳ በጊዜያዊነት አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራት የቀድሞ ተጫዋቾች ቀርቦበት በነበረው ክስ በፊፋ ጥሎበት የነበረው የተጫዋቾች...