የዋልያዎቹ የማክሰኞ ጨዋታ የት ይካሄድ ይሆን ?

 

በመጪው ማክሰኞ በ ባህርዳር አለም አቀፍ ስታዲየም አራተኛ የምድብ ጨዋታቸውን ከ ኒጀር ጋር እንደሚያካሂዱ ቀነ ቀጠሮ ቢያዝም በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ ጨዋታው ወደ ሌላ ስታዲየም ለማዞር ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል ።

ይህንንም ተከትሎ በዕለተ ማክሰኞ ሊካሄድ የታቀደው መርሐ ግብር በ አዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታውን ለማካሄድ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ከታማኝ የፌዴሬሽን ምንጮች ለማረጋገጥ ችለናል ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአሁን ሰዓት ከ ኒጀር ወደ ኢትዮጵያ በማቅናት ላይ ሲገኙ አመሻሹን አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor