ያለፉትን ሁለት ጨዋታዎች በተመሳሳይ አንድ ለዜሮ በሆነ ዉጤት ማሸነፍ የቻሉት ቡናማዎቹ ሶስተኛ ተከታታይ ድላቸዉን ለማስመዝገብ ጠንካራ ፉክክር ባደረጉበት ጨዋታ የመሳይ ተፈሪዉን አርባምንጭ ከተማ በሆነ ዉጤት ማሸነፍ ችለዋል።
ገና በጨዋታዉ የመጀመሪያ ደቂቃ ላይ የተጀመረውን ኳስ በቀኝ መስመር በኩል መሀመድ ኑር ናስር ወደ እየገፋ ወደ ሳጥን በገባበት ወቅት ጥፋት በመሰራቱ ምክንያት የተሰጠዉን ፍፁም ቅጣት ምት የፊት መስመር አጥቂዉ ብሩክ በየነ ቢመታዉም ኳሱ ኢላማዉን ሳይጠብቅ ወደ ዉጭ ወጥቷል። በ25ኛዉ ደቂቃ ላይ የግራ መስመር ተከላካዩ ሃይለሚካኤል አደፍርስ ያሻማውን ኳስ የፊት መስመር ተጫዋቹ ብሩክ በየነ በጭንቅላቱ ወደ ግብነት በመቀየር ክለቡን መሪ ማድረግ ችሏል።
- ማሰታውቂያ -
ከግቧ መቆጠር በኋላ የማጥቃት ሀይላቸዉን አጠናክረዉ የቀጠሉት ቡናማዎቹ ምንም እንኳን ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ለማድረግ ቢቸገሩም በኳስ ቁጥጥሩ ረገድ የተሻሉ ነበሩ ማለት ይቻላል። በተቃራኒው ግብ ካስተናገዱ በኋላ በቶሎ የተጫዋቾችን ቅያሪ በማድረግ ጥሩ ለመንቀሳቀስ የሞከሩት አዞዎቹ በተቃራኒው ሁለተኛ ግብ አስተናግደዋል። በዚህም የአርባምንጭ ተከላካዮች የሰሩትን ስህተት ተጠቅሞ የፊት መስመር ተጫዋቹ ብሩክ በየነ በየነ ያቀበለዉን ኳስ አጥቂዉ አንተነህ ተፈራ በግራ ዕግሩ ወደ ግብነት በመቀየር የቡናማዎቹን መሪነት ወደ ሁለት ለዜሮ ከፍ ማድረግ ችሏል።
ከዕረፍት መልስ በጥቂቱም ቢሆን ተሻሽለዉ ወደ ሜዳ የተመለሱት አርባምንጭ ከተማዎች በ49ኛዉ ደቂቃ ላይ ጥሩ ለግብ የቀረበ ሙከራ ማድረግ ችለዉ ነበር በዚህም የፊት መስመር ተጫዋቹ በላይ ከቀኝ መስመር በኩል የተሻገረለትን ኳስ ቀጥታ ወደ ግብ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም ግብ ጠባቂዉ በረከት እንደምንም ተቆጣጥሯል።
ከሁለት ደቂቃዎች በኋላ ደግሞ ኢትዮጵያ ቡናዎች ጥሩ የማግባት ዕድል አግኝተዉ ነበር በዚህም አማካዩ አማኑኤል ዮሐንስ የሰነጠቀለትን ኳስ አብዱልሀፊዝ ቶፊቅ ሳይጠቀምበት ቀረ እንጅ ምንአልባትም የቡናማዎቹን መሪነት ወደ ሶስት ከፍ ማድረግ የሚቻልበት አጋጣሚ ነበር።
በ62ኛዉ ደቂቃ ላይ አጥቂዉ ከርቀት ጥሩ ሙከራ ማድረግ ችሎ የነበረ ቢሆንም ኳሷ ለጥቂት በግቡ አናት ላይ ወጥታለች። በአንድ ደቂቃ በኋላ ደግሞ በፈጣን መልሶ ማጥቃት አርባምንጮች በቀኝ መስመር በኩል በተመስገን ደረሰ አማካኝነት ድንቅ ሙከራን ማድረግ ችለዉ የነበረ ቢሆንም በግብ ዘቡ በረከት አማረ አማካኝነት መክሸፍ ችሏል።
የጨዋታው ደቂቃ እየገፋ በመጣ ቁጥር ተፅዕኗቸዉ እየጨመረ የመጡት አዞዎቹ በ72ኛዉ ደቂቃ ላይ ጥሩ ዕድል ማግኘት ችለዉ ነበር በዚህም ከተከላካይ መስመር የተሻገረለትን ኳስ የፈመት መስመር አጥቁዉ ኳሷን ተቆጣጥሮ እየገፉ ሳጥን ዉስጥ ደርሶ ወደ ግብ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም በዕለቱ ድንቅ በነበረዉ ግብ ጠባቂ በረከት አማረ አማካኝነት ተጥቂት ወደ ዉጭ ወጥቶባቸዋል።
ወደ ጨዋታዉ መገባደጃ ወቅት በቁጥር በርከት ብለዉ በተቃራኒ ቡድን የሜዳ ክፍል ላይ በመገኘት የማጥቃት ሀይላቸዉን አጠንክረዉ መጫወት ችለዉ የነበሩት አዞዎቹ ምንም እንኳን ጥሩ ጥሩ ሙከራዎችን ማድረግ ችለዉ የነበረ ቢሆንም ዉጥናቸዉ ግብ ማስቆጠር ሳይቸሉ ጨዋታዉ በኢትዮጵያ ቡና 2ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።