ከዚህ ቀደም ደቡብ ሲቲ ካፕ በሚል ስያሜ በደቡብ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት ሲደረግ የነበረው የአቋም መፈተሻ ውድድር ዘንድሮ ስያሜውን እና አዘጋጅ ፌዴሬሽኑን ቀይሮ በሀዋሳ ከተማ ይካሄዳል ።
ሲዳማ ካፕ የሚል ስያሜ በተሰጠው ውድድር ላይ ስምንት ክለቦች የሚሳተፉ ይሆናል ። መቀመጫቸውን ሀዋሳ ያደረጉትን ሲዳማ ቡና እና ሀዋሳ ከተማን ጨምሮ ኢትዮጵያ ቡና ፤ ባህር ዳር ከተማ ፤ ድሬደዋ ከተማ ፤ ሰበታ ከተማ ፤ ሀዲያ ሆሳዕና ፤ ወልቂጤ ከተማ እና ወላይታ ዲቻ በውድድሩ ተሳታፊ የሚሆኑ ክለቦች ናቸው ።