የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ23ኛ ሳምንት ቀሪ የምድብ ‘ሀ’ እና የምድብ ‘ሐ’ ጨዋታዎች በዛሬው እለት በሁለት ከተሞች የተካሄዱ ሲሆን ከአንድ ጨዋታ በስተቀር ሁሉም ጨዋታዎች በአቻ ዉጤት ተጠናቀዋል።
በአሰላ ከተማ የተካሄደዉ የምድብ ‘ሀ’ ጨዋታዎች ዉጤት።
ሀሙስ ሚያዝያ 26
ሀላባ ከተማ 0-0 አዲስ ከተማ ክ/ከተማ
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 0-0 ቤንች ማጂ ቡና
ሰበታ ከተማ 1-1 ሰንዳፋ በኬ
- ማሰታውቂያ -
በባቱ ከተማ የተካሄደዉ የምድብ ‘ሐ’ ጨዋታዎች ዉጤት።
ደሴ ከተማ 0-0 የካ ክ/ከተማ
ነገሌ አርሲ 3-3 ሀምበሪቾ ዱራሜ
ኮልፌ ቀራንዮ 3-2 ዳሞት ከተማ
ምድብ ‘ሀ’ ን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ51 ነጥብ እየመራ የሚገኝ ሲሆን ምድብ ‘ለ’ ን አስቀድሞ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ማደጉን ያረጋገጠዉ ሻሸመኔ ከተማ በ47 ነጥብ እየመራ የሚገኝ ሲሆን ምድብ ‘ሐ’ ን ደግሞ ገላን ከተማ በ43 ነጥብ እየመራ ይገኛል።