የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ1ኛ ሊግ ክለቦች የ2015 ዓ.ም የውድድር ደንብ ውይይትና የእጣ ማውጣት ስነስርዓት በዛሬው እለት ጥቅምት 29 ተከናውኗል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የአንደኛ ሊግ ኮሚቴ ስብሳቢ አቶ አሰር ኢብራሂም የ1ኛ ሊግ ክለቦች የ2015 ዓ.ም የውድድር ደንብ ውይይትና የእጣ ማውጣት ስነስርዓት መክፈቻ ባደረጉት ንግግር “እንኳን ለ2015 ዓ.ም የውድድር ዘመን በሰላም አደረሳችሁ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 1ኛ ሊግ የ2014 ዓ.ም ውድድር በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። በዚህ ዓመትም ለየት ባለ መልኩ እናከናውናለን። በስራ አስፈፃሚ ደረጃ በተነጋገርነው መሰረት ውጤታማ ስፖርታዊ ጨዋነት የሰፈነበትና ተተኪ ተጫዋችች ማፍራት ላይ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን። ያለፈው አመት የነበሩትን ክፍተቶች በማረም ጠንካራ ጎኖችን በማጎልበት እንሰራለን።” ብለዋል።
የ 2014 ዓ.ም የውድድር አፈፃፀም ሪፖርትና የዳኞች ሪፖርት የቀረበ ሲሆን የ 2015 ዓ.ም የውድድር ደንብ በተለይም የተሻሻሉ ደንቦች ላይ በአቶ ቡዛየሁ ጌታቸው ቀርቦ ውይይት ተየርጎበታል። ውይይቱንም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሐፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን
፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የ 1ኛ ሊግ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አሰር ኢብራሂም ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የውድድር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ከበደ ወርቁ እንዲሁም የአንደኛ ሊግ ኮሚቴ አባል አቶ አቶ ብዙአየሁ ጌታቸው በመሆን የመሩት ሲሆን ከተሰብሳቢዎች ለቀረቡ ጥያቄዎችም ምላሽ ተሰጥቷል።
በመጨረሻም ለውድድሩ የሚያስፈልገውን መስፈርት ባሟሉ 29 ቡድኖች መከከል የምድብ ድልድልና የእጣ ማውጣት ስነስርዓት ተከናውኗል።
በፕሮግራሙ ላይ በመገኘት የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ “1ኛ ሊጉ ከፍተኛ ፉክክር የሚታይበት ቦታ ነው። የወጣቶች ልማት ላይ ትኩረት ሰጥታችሁ መሥራት አለባችሁ። ብትችሉ በዋናው ቡድን በየዓመቱ ሁለት ሦስት በቋሚ አሰላለፍ ማሰለፍ ብትችሉ በዚህ መልኩ አስተዋፅኦ ማድረግ ትችላላችሁ። ለብሄራዊ ቡድን የሚሆኑ ተጫዋቾች ማፍራት ምስጋናው የናንተ ነው። መልካም የውድድር ዘመን ይሁንላችሁ።” ብለዋል።
የ 1ኛ ሊግ ክለቦች አስፈላጊውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጨማሪ ክለቦች እስከ ህዳር 9 ምዝገባ ተከናውኖ ተወካዮች በተገኙበት ህዳር 10 2015 ዓ.ም በየምድቡ የሚደለደሉ ሲሆን የቡድኖቹ ቁጥር ታይቶ አምስተኛ ምድብ ሊኖር እንደሚችል ተገልጿል።
ዛሬ በተካሄደ የምድብ ድልድል የእጣ ማውጣት ስነ ስርአት ቡድኖች በሚከተለው መልኩ ተደልድለዋል።
ምድብ 1
1. ሙከ ጡሪ ከተማ
2. ድሬ ባፋኖ
3. አዴት ከተማ
4. ቢሾፍቱ ከተማ
5. አዲስ አበባ ፖሊስ
6. ዱከም ከተማ
7. ድሬዳዋ ፖሊስ
8. ዳንግላ ከተማ
ምድብ 2
1. አማራ ውሃ ሥራዎች ድርጅት
2. ቅበት ከተማ
3. ሞጆ ከተማ
4. ወሊሶ ከተማ
5. ወንዶ ገነት ከተማ
6. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
7. ካራማራ
8. አማራ ፖሊስ
ምድብ 3
1. ሱሉልታ ከተማ
2. ሆለታ ከተማ
3. ልደታ ክፍለ ከተማ
4. ቡሬ ዳሞት
5. አዲስ ቅዳም
6. ሐረር ከተማ
7. አረካ ከተማ
ምድብ 4
1. ሞጣ ከተማ
2 ሰመራ ዩኒቨርሲቲ
3. በደሌ ከተማ
4. ደባርቅ ከተማ
5. ሾኔ ከተማ
6. ኦሮሚያ ፖሊስ