መነሻ ገጽ ሀዲያ ሆሳዕና የጨዋታ ዘገባ | የተመስገን ብርሀኑ የተጨማሪ ደቂቃ ግብ ሀድያ ሆሳዕናን ለድል አብቅቷል
ሀዲያ ሆሳዕናለገጣፎ ለገዳዲዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | የተመስገን ብርሀኑ የተጨማሪ ደቂቃ ግብ ሀድያ ሆሳዕናን ለድል አብቅቷል

አጋራ
አጋራ

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የስድስተኛ ሳምንት መርሀ ግብር የመጨረሻ ጨዋታ ሀድያ ሆሳዕና ነጥቡን ከመሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያስተካከለበትን ውጤት አስመዝግቧል ።

በሀድያ ሆሳዕና በኩል በአምስተኛው ሳምንት ወላይታ ድቻን ባሸነፉበት ጨዋታ ላይ ከነበረው የመጀመሪያ አሰላለፍ አንድ ለውጥ ብቻ አድርገው የገቡ ሲሆን ፀጋዬ ብርሀኑ ሰመረ ሀፍተይን ተክቶ የተሰለፈ ተጫዋች ነው ። በለገጣፎ ለገዳዲ በኩል ደግሞ በሳምንቱ በባህርዳር ከተማ በተረቱበት ጨዋታ ላይ ከተጠቀሙት ምርጥ 11 ሁለት ለውጦትችን በማድረግ ፍቅሩ አለማየሁን እና አንዋር አብዱልጀባር በበረከት ተሰማ እና ኦካይ ጁል ምትክ አሰልፈዋል ።

በመጀመሪያው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሀድያ ሆሳዕና አንፃራዊ የበላይነት የነበራቸው ሲሆን በተለይም በሁለቱ ክንፎች በኩል የለገጣፎ ለገዳዲን መረብ ለማግኘት ጥረዋል ።

በለገጣፎ ለገዳዲ በኩል በቀጥተኛ ኳሶች ወደ ተገጣሚያቸው የግብ ክልሎች ለመድረስ የሞከሩ ሲሆን አጥቂው ካርሎስ ዳምጠውን ኢላማ ያደረጉ ተደጋጋሚ ኳሶችም ወደፊት ይላኩ ነበር ።

በጨዋታው የመጀመሪያ የግብ ሙከራ በ2ኛው ደቂቃ ላይ ሲመዘገብ ለገጣፎ ለገዳዲዎች ያገኙትን የቅጣት ምት ኪሩቤል ወንድሙ በቀጥታ ወደ ግብ ሞክሮ በግብ ጠባቂው ፔፔ ሰይዶ ተይዞበታል ።

ሀድያ ሆሳዕናዎች በጨዋታው የግብ ዕድል ለመፍጠር ተቸግረው የቆዩ ሲሆን ቀዳሚ የግብ ሙከራቸውን በ25ኛው ደቂቃ ላይ አድርገዋል ። ባዬ ገዛኸኝ በረጅም የደረሰውን ኳስ እየገፋ ሄድ አስቆጠረው ተብሎ ሲጠበቅ ከፍ አድርጎ ወደ ግብ የላከው ኳስ ከግቡ አናት በላይ ወጥቷል ።

በጨዋታው በሁለቱም በኩል መሪ ለመሆን ጥረቶችን ቢያሳዩም የግብ ሙከራዎች አለመኖራቸው ጨዋታውን ለዕይታ ሳቢ እንዳይሆን አድርጎታል ።

የመጀመሪያው አጋማሽ መጠናቀቂያ ደቂቃዎች ላይ ተፈራ አንለይ በረጅም የተላከለትን ኳስ የሀድያ ሆሳዕና ተከላካይን አልፎ ክግብ ጠባቂው ጋር መገናኘት ችሎ የነበረ ቢሆንም ዕድሉን ሳየጠቀምበት ቀርቷል ።

የመጀመሪያው አጋማሽም ያለ ግብ ፍፃሜውን አግኝቷል ።

በሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በሁለቱም ተጋጣሚዎች በኩል ከጨዋታዉ ሶስት ነጥብ ይዘው ለመውጣት ጥረቶችን ያደረጉበት ነበር ። በአጋማሹ ምንም እንኳን በኳስ ቁጥጥሩ ረገድ ሀድያ ሆሳዕናች የተሻሉ የነበሩ ቢሆንም ወደ ግብ በመድረሱ ረገድ ለገጣፎ ለገዳዲዎች አንፃራዊ የበላይነት ነበራቸው ።

በ57ኛው ደቂቃ ላይ ከቅጣት ምት ወደ ግብ የተሻገረውን ኳስ መሀመድ አበራ በግንባር ገጭቶ ለማስቆጠር ያደረገው ጥረት ሳይሰምር ቀርቷል ።

ከአራት ደቂቃዎች በኋላ ካርሎስ ዳምጠው ጥሩ አቋቋም ላይ ሆኖ የደረሰውን ኳስ የመቆጣጠር ስህተቱ ታክሎበት በሳጥን ውስጥ ግብ ጠባቂውን አልፎ ለማስቆጠር ቢጥርሞ ሳይሳካለት ቀርቷል ። በአጋጣሚው ለገጣፎ ለገዳዲዎች የፍፁም ቅጣት ምት ይገባናል ቢሉም የዕለቱ የመሀል ዳኛ በዝምታ አልፈውታል ።

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የሀድያ ሆሳዕናው ግብ ጠባቂ ኳስ በረጅም ለማውጣት ሲሞክር ካርሎስ ዳምጠው ነጥቆት የነበረ ቢሆንም አጥቂው ወርቃማውን አጋጣሚ አምክኖታል ።

ሀድያ ሆሳዕናዎች በ76ኛው ደቂቃ ላይ የጨዋታው የመጀመሪያ ኢላማውን የጠበቀ የግብ ሙከራ አድርገዋል ። አምበሉ ወርቅይታደስ አበበ ከሳጥን ውጪ አክርሮ ወደ ግብ የመታውን ኳስ ግብጠባቂው ወንድወሰን መልሶታል ።

መደበኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጠናቆ አምስት ያህል ደቂቃዎች የተጨመሩ ሲሆን በነዚልዠህ ደቂቃዎች ላይ የለገጣፎ ለገዳዲዎቹ ወንድወሰን ገረመው እና መዝገቡ ቶላ መጋጨታቸውን ተከትሎ መዝገቡ ጨዋታውን መቀጠል ሳይችል ቀርቷል ። የተጫዋቾች ቅያሪ አድርገው ጨርሰው የነበሩት ለገጣፎ ለገዳዲዎች ቀሪዎቹን ደቂቃዎች በጎዶሎ ለመጫወት ተገደዋል ።

ተጨማሪ ደቂቃዎች አልፈው የዳኛው የጨዋታ መጠናቀቂያ ፊሽካ ድምፅ ሲጠበቅ ሀድያ ሆሳዕናዎች ተቀይሮ በገባው ተመስገን ብርሀኑ ግብ ከጨዋታው ሶስት ነጥብ ይዘው ወጥተዋል ።

ሀድያ ሆሳዕናዎች ደሰታቸውን ከገለፁ በኋላ ከዳኛው ጋር አላስፈላጊ ንትርክ ውሰጥ ገብቶ የነበረው ግርማ በቀለ በቀጥታ የቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...