ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች
ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ያገኛሉ
*…. የፋሲል ከነማው አምሳሉ ጥላሁን ” ምንም የማይወጣልኝ ልቅም ያልኩ ቆንጆ ነኝ” ይላል…..”ግብአስቆጥሬ ያለቀስኩት የወጣቶች ህይወት መቀጠፉ ያብቃ የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ነው” ሲልም የእውነት ትልቅ ቁምነገር ያለው መልዕክት አስተላልፏል።
*…. ከነገ በስቲያ እሁድ 9 ሰአት ፋሲል ከነማና ቅዱስ ጊዮርጊስ ይጫወታሉ….
“ቅ/ጊዮርጊሶች እኛ ላይ ለመድረስ ሲሉ ተጨናንቀው ስለሚገቡ እናሸንፋቸዋለን”
በማለት የፋሲሉ በረከት ደስታ ሲናገር የፈረሰኞቹ አምበል ጌታነህ ከበደ በበኩሉ
“የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ የማንሳት ጉዟችንን ፋሲል ከነማን በመርታት እናስቀጥላለን” ሲል ፎክሯል።
*……የኢትዮጵያ ቡናው ሃይሌ ገብረ ተንሳይ፣ የባህርዳር ከተማው ሳሙኤል ተስፋዬና የሀዲያ ሆሳዕናው ተስፋዬ በቀለ /ጃምቦ/ ስለአንደኛ ዙር ሂደትና በሁለተኛው ዙር ቡድኖቻቸው በምን አይነት መልኩ እንደሚቀርቡና ለሻምፒዮናነት ስላላቸው ዕድል ለሃትሪክ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
*….በዩሮፓ ሊግ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን ተከትሎ የመድፈኞቹ የግብ ቀበኛ ፒየር ኤምሬክ ኦባምያንግ
“የውድድር ዘመኑን ታላቅ ድል በቤኔፊካ ላይ ተቀዳጅተናል”ሲል የተሰማውን ደስታ ተንፍሷል።
ከዚህም ውጪ……
በውጪ ዘገባዎቻችን
*…እያደር እንደ ወይን እየጣፈጠ ስላለው
የቸልሲው ኦሊቪዬ ዢሩ…..
*…ስለማን.ዩናይትዱ የመጪው ዘመን
ተስፋ አማድ ዳኒሎ….የምንሎት መረጃዎች አሉን…..
ቅዳሜና እሁዳችሁ
የተባረከ ይሁን……
https://www.hatricksport.net/
አስተያየት ይስጡ