ፊፋ በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ኮንግረስ አስመልክቶ ልዑክ ቡድኑን አዲስ አበባ ላከ

ኢትዮጵያ 70ኛው የፊፋ አባል ሀገራት ስብሰባን በግንቦት ወር መጨረሻ በአዲስ አበባ እንደምታካሂድ ይታወቃል፡፡ ይህንንም ተከትሎ አለማቀፉ የእግር ኳስ ማህበር(ፊፋ) የተለያዩ የልዑካን ቡድን አባላትን በመላክ 70ኛው የፊፋ ኮንግረስ ውጤታማ ማድረግ በሚችልበት ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ማካሄዱ ይታወሳል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም ይህ ትልቅ ፕሮግራምን ውጤታማ ለማድረግ ከኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመሆን በኢፌዴሪ ክብርት ፕሬዝዳንት የበላይ ጠባቂነት የሚመራ ብሄራዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ ከተገባ እነሆ ሁለት ወራት ተቆጥረዋል፡፡

ከሰኞ የካቲት 16/2012ዓ.ም አዲስ አበባ የከተመው 20 አባላት ያሉት የፊፋ ልዑክ ቡድን 70ኛው የፊፋ ኮንግረስ በሚካሄድብት የአፍሪካ ህበረት ጽ/ቤት በመገኘት 70ኛው የፊፋ ኮንግረስ ብሄራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር በተለያዩ ጉደዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፤ በውይይቱ ብሄራዊ አስተባባሪው ከመሰረታቸው ሰባት ንዑስ ኮሚቴዎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከአፍሪካ ህብረት አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ ውይይቱም ስብሰባው ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ውጤታማ ማድረግ በሚቻለበት ጉዳይ ዙሪያ ያጠነጠነ ሲሆን፤ በአፍሪካ ህብረት የሚካሄዱ የሀገራት መሪዎች ስብሰባ በምን መልኩ ሲደረግ እንደቆየ ልምድ የተለዋወጡበት እና በስብሰባው ጊዜ የአፍሪካ ህበረት ጽ/ቤት የግቢ ገጽታ ምን ሊመስል እንደሚገባ የጉባዔው ተሳታፊዎች በሚስተናገዱበት ዙሪያ የተደረገ ውይይት ነው፡፡
እንዲሁም የቪዛ ሂደቱ፤ የጋዜጠኞች በስብሰባው ለመሳተፍ ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች እና ለስብሰባው አስፈላጊ የሚሆኑ እቃዎች ወደ ኢትዮጵያ በሚገቡበት ሁኔታ ዙሪያ ውይይት የተካሄደበት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከኤርፖርት ጀምሮ እሰከ ሆቴል ብሎም እሰከ ስብሰባ ቦታ ድረስ የፕሮቶኮል ስራው እና የደህነንነት አጠባበቁ ምን ሊሆን እንደሚገባ ብሎም ያለው ልምድ ምን እንደሚመስል ውይይት የተደረገበት ነው፡፡

በሀገራት የፌዴሬሽን ፕሬዝዳንቶች መካከል የሚካሄደው የእግር ኳስ ውድድር እና ጋዜጣዊ መግለጫዎች በምን መልኩ ሊሰተናገዱ እንደሚገባ አቅጣጫ የተሰጠበት ከመሆኑም በተጨማሪ የተሳትፎ የምዝገባ ሂደቱ በምን ወር ተጀምሮ በየትኛው ወር ይጠናቀቃል የሚለው የፊፋ ምክረ ሀሳብ የቀረበበት ነው፡፡ለስብሰባው አስፈላጊ የሆኑ ማቴሪያሎች ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን ጋር በመነጋገር ወደ ኢትዮጵያ መግባት የሚችሉብት ፈቃድ በምን መልኩ መስተናገድ እንዳለበት ውይይት ተካሂዷል፡፡ የፊፋ ልዑክ ቡድን አባላት ከተለያዩ ተቋማት የስራ ሃላፊዎች ጋር በጋራ አንዲሁም በተናጥል ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

via- EFF

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor