ወጣት ተጨዋቾች ላይ ትኩረት አድርገው እየተንቀሳቀሱ ሚገኙት ደደቢቶች የአራት ተጨዋቾችን ፊርማ አጠናቀዋል።በክረምቱ 8 ተጨዋቾችን ያስፈረመው ደደቢት አሌክሳንደር ዓወት፣ሐዱሽ በርሀ፣ረሺድ ማታውሲ ና ሙሉጌታ ብርሃነ(ሻኩር) አስፈርሟል።
በትግራይ ዋንጫ የውድድሩ ኮከብ ግብ ጠባቂ ሽልማትን ያገኘው ረሺድ ማታውሲ ከክለቡ ጋር የተሳካ ሙከራ ጊዜ ማሳለፋን ተከትሎ ሰመያዊዮቹን በቀዋሚነት መቀላቀል ችሏል።በተጨማሪ የደደቢት ተስፋ ቡድን ውጤት የሆነው ግብ ጠባቂው ሐዱሽ በርሄ ከትግራይ ውሃ ስራዎች ደደቢትን በመቀላቀል የረሺድ ጥሩ ምትክ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።
በ2009 ከሃዋሳ ከተማ 20 ዓመት በታች ቡድን ጋር በመሆን የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግን በኮከብ ጎል ኣግቢነት ያጠናቀቀው ወጣት አጥቂው አሌክሳንደር ዓወት ከቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ደደቢትን ሲቀላቀል በተመሳሳይ ደደቢቶች በኣጥቂ ቦታ ያላቸውን አማራጭ ለማስፋት ሙሉጌታ ብርሃነ(ቻኩር) ማስፈረም ችለዋል።