በመስከረም ወር አንድ የወዳጅነት ጨዋታን ጨምሮ አራት ጨዋታዎችን ያደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በኬንያ አቻው በደርሶ መልስ 3-0 መሸነፉን ተከትሎ አንድ ደረጃ ወደታች ዝቅ በማለት 150ኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገዷል፡፡
በባለፈው ወር የሃገራት ደረጃ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 149 የነበረ ሲሆን ደረጃውን ለሚጢጢዋ አፍሪካዊ ደሴት ኮሞሮስ አስረክቦ አንድ ደረጃ ቁልቁል ወርዷል፡፡
የባለፈውን ወር የፊፋ የሃገራት ደረጃ ቁንጮ ከፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን ጋር በጋራ ተቆናጥጣ የነበረችው ቤልጂየም በዚህ ወር መሪነቱን ለብቻዬ ብላለች፤ የአፍሪካ ሃገራትን ፊት አውራሪነት የምትመራው ሴኔጋል ከዓለም 25ኛ ደረጃ ላይ ተገኝታለች፡፡