መነሻ ገጽ መቐለ 70 እንደርታ የጨዋታ ቅድመ-ዕይታ | ጅማ አባጅፋር ከ መቐለ 70 እንደርታ
መቐለ 70 እንደርታዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግጅማ አባጅፋር

የጨዋታ ቅድመ-ዕይታ | ጅማ አባጅፋር ከ መቐለ 70 እንደርታ

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ነገ(እሁድ) 7 ጨዋታዎችን ያስተናግዳል። በጅማ ዩኒቨርሲቲ ስታድየም ሚካሄደው የጅማ አባጅፋርና መቐለ 70 እንደርታ ጨዋታ እንደሚከተለው ዳሰነዋል።

ጨዋታ: ጅማ አባጅፋር ከ መቐለ 70 እንደርታ
የጨዋታ ቀን: እሁድ ጥር 24/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ፌደራል ዳኛ ማኑሄ ወልደፃዲቅ 
የጨዋታ ቦታ: ትግራይ ስታድየም

በ12ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሊጉ መሪ መቐለ 70 እንደርታ ወደ ጅማ ተጉዞ ወራጅ ቀጠና ላይ ሚገኘውን ጅማ አባጅፋርን ይገጥማል።ምዓም አናብስቶቹ መሪነታቸውን ለማስቀጠል ጅማዎች ከወራጅ ቀጠናው ለመውጣት ሁለቱም ቡድኖች ጥንቃቄ የታከለበት አጨዋወትን ሊመርጡ እንደሚችሉ ይገመታል።

በሜዳቸው ሚያካሂድዋቸውን ጨዋታዎች በተለየ አቀራረብ ለመግባት ሚሞክሩት ጅማዎች ጥንቃቄ ኤልያስ መሐመድና ኤርሚያስ ኃይሉ ላይ መሰረት ያደረገ የማጥቃት አጨዋወትን በመጠቀም እድሎችን ሊፈጥሩ ይችላሉ።በመከላከሉ ረገድ ማይታሙት ጅማዎች ግብ ሊሆኑ ሚችሉ እድሎችን በመፍጠር ላይ ያሉባቸው ችግሮች እንዲሁም አልፎ አልፎ ሚገኙትን የግብ አጋጣሚዎች በአግባቡ አለመጠቀማቸው ቡድኑ ጨዋታዎችን አሸንፎ እንዳይወጣ እንቅፋቶች ሆነውታል።

በቅጣት እና በጉዳት ወሳኝ ተጨዋቾቻቸውን ኦኪኪ ኦፎላቢ፣ዮናስ ገረመው፣ያሬድ ከበደ፣ስዩም ተስፋዬን ለነገው ጨዋታ ያጡት መቐለዎች ከፍተኛ ፈተና ይጠብቃቸዋል።በተለይ ከጉዳት ከተመለሰ በኃላ መሀል ላይ የቡድኑ ወሳኝ ተጨዋች የነበረው ዮናስ ገረመውን ማጣታቸው አጨዋወታቸው ላይ ብዙ ለውጦችን እንዲያደርጉ ሊያስገድዳቸው ይችላል።

የመጀመርያ ሁለት የሜዳ ጨዋታዎቻቸውን ከባለፈው የውድድር ዓመት በቀጠለ ቅጣት አዳማ ላይ የተጫወቱት ጅማዎች ቅጣቱን ከጨረሱ በኃላ በሜዳቸው 4 ጨዋታዎችን አካሂደው 7 ነጥቦችን ማሳካት ችለዋል።

ከሜዳቸው ውጪ 5 አምስት ጨዋታዎችን ያካሄዱት መቐለዎች ከሌሎች የፕሪምየር ሊግ ክለቦች አንፃር ከሜዳቸው ውጪ ጥሩ ክብረ ወሰን ያላቸው ቢሆንም በነገው ጨዋታ ወሳኝ ተጨዋቾቻቸውን በጉዳት እና በቅጣት ማጣታቸው በግምት ሲገባ ጨዋታው ሊከብዳቸው እንደሚችል ይገመታል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...