12ኛሳምንት የኢትዮጲያ ፕሪምየር ሊግ ቅዳሜ እና እሁድ በተለያዩ ከተሞች ቀጥሎ ይካሄዳል።በትግራይ ስቴዲየም ሚካሄደውን የስሑል ሽረ እና ሀዋሳ ከተማን ጨዋታ ቅድመ እይታ እንደሚከተለው ዳሰነዋል መልካም ንባብ።
ጨዋታ:ስሑል ሽረ ከ ሀዋሳ ከተማ
የጨዋታ ቀን: እሁድ ጥር 23/5/2012
የጨዋ ሰአት: 9:00
የጨዋታው አርቢትር: ፈደራል ዳኛ ተካልኝ ይልማ
የጨዋታው ቦታ: በትግራይ ስታድየም
በ11ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በትግራይ ደርቢ በሊጉ መሪ መቐለ 70እንድርታ ሽንፈትን ያስተናገዱት ስሑል ሽረዎች በሜዳው ወላይታ ድቻን አስተናግዶ በአለልኝ አዘነ የመጨረሻ ደቂቃ ግብ ሙሉ ሥስት ነጥብን ያገኘውን ሀዋሳ ከተማን በትግራይ ስታዲየም ያስተናግዳል።
ከተከታታይ 7 ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ጉዞ በኃላ በመቐለ 70 እንደርታ የተሸነፋት ስሑል ሽረዎች ወደ አሸናፊነት መንገድ ለመመለስ ማጥቃት ላይ መሰረት ያደርገ አጨዋወትን ይጠቀማሉ ተብሎ ይጠበቃል።መስመር ላይ መሰረት ያደርገ የማጥቃት እንቅስቃሴን ሚከተሉት ስሑል ሽረዎች ከሜዳው ውጪ ወደ ኃላ አፈግፍጎ ሚጫወተውን የሀዋሳ ከተማ ተከላካይ ክፍልን የማስከፈት ብርቱ ፈተና ሚጠብቃቸው ይሆናል።
- ማሰታውቂያ -
ወጥ የሆነ አቋም የማይታይባቸው እና ከሜዳቸው ውጪ የማሸነፍ ልምድ የሌላቸው ሀዋሳ ከተማዎች መከላከል ላይ ያመዘነ የጨዋታ ዘይቤ ይጠቀማሉ ተብሎ ይጠበቃል።ወሳኝ ተጨዋቾቻቸው እስራኤል እሸቱ እና መስፍን ታፈሰን በጉዳት ያጡት አሰልጣኝ አዲሴ ካሳ ከነገው ጨዋታ ነጥብ ለማግኘት ተደጋጋሚ ስህተቶችን ሚሳሳተውን የመሀል ክፍላቸውን በጥንቃቄ እንዲጫወት የማድረግ የቤት ስራ ይኖርባቸዋል።
በስሑል ሽረ በኩል ኮትዲቫራዊው የመስመር አጥቂ ዲድየ ሌብሪ ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር በነበራቸው ጨዋታ ቀይ ካርድ በመመልከቱ፣ኡጋንዳዊው ያሰር ሙገርዋ በበኩሉ የተጠናቀቀው ውሉን የማራዘም ሂደት አለመጨረሱን ተከትሎ በነገው ጨዋታ ቡድናቸውን የማያገለግሉ ሲሆን ፣በሀዋሳዎች በኩል ደግሞ ወጣቱ አጥቂ መስፍን ታፈሰ እና እስራኤል እሸቱ በጉዳት ማይሰለፋ ይሆናል።
ባለሜዳዎቹ በ2011 ወደ ሊጉ ከመጡ በኃላ ከሀዋሳ ከተማ ጋር 2 ያህል ጊዜ ሲገናኙ ሀዋሳ በሜዳው 6-1 በሆነ ሰፊ ውጤት ሲረታ ባንፃሩ ስሑላውያን ሽረ ስታድየም ላይ 4-0 አሸንፈዋል።
ሁለቱም ክለቦች እስካሁን ካደረጉት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች በእኩል 16 ነጥብ በእኩል የግብ እዳ 5ኛ እና 6ኛ ደረጃ ላይ መቀመጣቸው ጨዋታውን ይበልጥ አጓጊ ያደርገዋል።